ዘፍጥረት 34:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ከአባቱ ቤተ ሰብ ሁሉ እጅግ የተከበረው ይህ ወጣት የያዕቆብን ልጅ እጅግ ወድዷት ስለ ነበር፣ ያሉትን ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ወጣቱም ልጅ፥ የያዕቆብን ልጅ ወድዶአልና፥ ያሉትን ያደርግ ዘንድ አልዘገየም። እርሱም በአባቱ ቤት ካሉት ሁሉ የከበረ ነበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 ሴኬም፥ የያዕቆብን ልጅ እጅግ ወዶአት ስለ ነበር የተነገረውን ሁሉ ለማድረግ ምንም ጊዜ አልወሰደበትም፤ ከዚህም በላይ በቤተሰቡ ውስጥ እጅግ የተከበረ በመሆኑ የፈለገውን ለማድረግ መብት ነበረው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ብላቴናውም ይህን ነገር ያደርግ ዘንድ አልዘገየም፤ የያዕቆብን ልጅ ወድዶአልና፤ እርሱም ከአባቱ ቤተ ሰብእ ሁሉ የከበረ ነበረ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 ብላቴናውም ያሉትን ያደርግ ዘንድ አልዘገየም የያዕቆብን ልጅ ወደዶአልና እርሱም በአባቱ ቤት ካሉት ሁሉ የከበረ ነበረ። 参见章节 |