Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 34:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም፣ በእኅታቸው በዲና ላይ ስለ ተፈጸመው ነውር፣ የሆዳቸውን በሆዳቸው ይዘው፣ ለሴኬምና ለአባቱ ለኤሞር በተንኰል መልስ ሰጡ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የያዕቆብም ልጆች፥ እኅታቸውን ዲናን አርክሶአታልና፥ ለሴኬምና ለአባቱ ለኤሞር በተንኰል መለሱ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሴኬም እኅታቸውን ዲናን አስነውሮ ስለ ነበር የያዕቆብ ልጆች ለእርሱና ለአባቱ ለሐሞር በተንኰል እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ለሴ​ኬ​ምና ለአ​ባቱ ለኤ​ሞር በተ​ን​ኰል መለሱ፤ እኅ​ታ​ቸ​ውን ዲናን አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ታ​ልና፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የያዕቆብም ልጆች ለሴኬምና ለአባቱ ለኤሞር በተንኮል መለሱ እኅታቸውን ዲናን አርክሶአታልና፤

参见章节 复制




ዘፍጥረት 34:13
17 交叉引用  

ጥሎሽ ብትሉኝ ጥሎሽ፣ ስጦታ ብትሉም የፈለጋችሁትን ያህል እሰጣለሁ፤ ብቻ ልጅቱን እንዳገባ ፍቀዱልኝ።”


እንዲህም አሏቸው፤ “እኅታችንን ላልተገረዘ ሰው ብንሰጥ ውርደት ስለሚሆንብን፣ እንዲህ ያለውን ነገር አናደርገውም።


እናንተ ግን፣ በሐሰት የምትለብጡ ናችሁ፤ ሁላችሁ የማትረቡ ሐኪሞች ሆናችኋል።


ለእግዚአብሔር ብላችሁ በክፋት ትናገራላችሁን? ስለ እርሱስ በማታለል ታወራላችሁን?


እርስ በርሳቸው ውሸት ይነጋገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈርና በሁለት ልብ ይናገራሉ።


ክፉ ሰው በክፉ ንግግሩ ይጠመዳል፤ ጻድቅ ሰው ግን ከመከራ ያመልጣል።


በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀናል፤ ሐሰት ተናግረናል፤ አምላካችንን ከመከተል ዘወር ብለናል፤ ዐመፃንና ግፍን አውርተናል፤ ልባችን የፀነሰውን ውሸት ተናግረናል።


የሚታመን ሰው ከምድር ጠፍቷል፤ አንድም እንኳ ቅን ሰው የለም፤ ሰው ሁሉ ደም ለማፍሰስ ያደባል፤ እያንዳንዱም ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል።


እንዲህ አሏቸው፤ “ ‘ተኝተን ሳለን ደቀ መዛሙርቱ በሌሊት መጥተው ሰረቁት’ በሉ፤


ወዳጆቼ ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ቍጣ ፈንታ ስጡ እንጂ አትበቀሉ፤ ጌታ “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” እንዳለ ተጽፏልና።


ማንም በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን እርስ በርሳችሁም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁልጊዜ መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ተጣጣሩ።


ሳምሶንም መልሶ፣ “ከእንግዲህ በፍልስጥኤማውያን ላይ በሚደርሰው ጕዳት ተጠያቂ አልሆንም” አላቸው።


跟着我们:

广告


广告