Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 31:55 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

55 በማግስቱም ማለዳ ላባ የልጅ ልጆቹን እንዲሁም ሴቶች ልጆቹን ስሞ መረቃቸው፤ ከዚያም ወደ አገሩ ተመለሰ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

55 ጠዋት በማለዳ ላባ ተነሥቶ የልጅ ልጆቹን እና ሴቶቹን ልጆቹን ሳመ ባረካቸውም፥ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

55 በማግስቱ ላባ ጥዋት በማለዳ ተነሥቶ ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን በመሳምና በመመረቅ ተሰናበታቸው፤ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

55 ላባም ማልዶ ተነ​ሥቶ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን ልጆ​ቹን ሳመ፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም፤ ላባም ተመ​ልሶ ወደ ስፍ​ራው ሄደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

55 ላባም ማልዶ ተነሥቶ ወንዶቹንና ሴቶቹን ልጆቹን ሳመ ባረካቸውም ላባም ተመልሶ ወደ ስፍራው ሄደ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 31:55
18 交叉引用  

እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋራ ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ቤቱ ተመለሰ።


ርብቃንም እንዲህ ብለው መረቋት፤ “እኅታችን ሆይ፤ እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽ የጠላቶቹን ደጆች ይውረስ”።


ይሥሐቅ ያዕቆብን አስጠርቶ ከመረቀው በኋላ፣ እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ምንም ቢሆን ከነዓናዊት ሴት አታግባ።


ራሔል ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፤ “ወደ ገዛ ቤቴ፣ ወደ አገሬ እንድመለስ አሰናብተኝ፤


የልጆቼን ልጆችና ልጆቼንም ስሜ ብሰናበት ምን ነበረበት? የሠራኸው የጅል ሥራ ነው።


ላባም ለያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ሴቶቹም፣ ልጆቹም የእኔው ልጆች ናቸው፣ መንጎቹም ቢሆኑ የራሴ ናቸው። ታዲያ፣ በእነዚህ ሴቶች ልጆቼና በወለዷቸው ልጆቻቸው ላይ ዛሬ ምን ማድረግ እችላለሁ?


ዔሳው ግን ሊገናኘው ወደ እርሱ ሮጦ ሄዶ ዐቀፈው፤ በዐንገቱም ላይ ተጠምጥሞ ሳመው፤ ሁለቱም ተላቀሱ።


ስለዚህም ሕዝቡ በሙሉ ዮርዳኖስን ተሻገረ፤ ከዚያ በኋላም ንጉሡ ተሻገረ። ንጉሡ ቤርዜሊን ስሞ መረቀው፤ ቤርዜሊም ወደ ቤቱ ተመለሰ።


ሰውን ብትቈጣ እንኳ ለክብርህ ይሆናል፤ ከቍጣ የተረፉትንም ትገታቸዋለህ።


የሰው መንገድ እግዚአብሔርን ደስ ሲያሠኘው፣ ጠላቶቹ እንኳ ዐብረውት በሰላም እንዲኖሩ ያደርጋል።


ባላቅም በለዓምን፣ “እንዴት እንዲህ ታደርገኛለህ? ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ አመጣሁህ፤ አንተ ግን ባረክሃቸው እንጂ ምንም አላደረግህልኝም!” አለው።


እግዚአብሔርም በበለዓም አፍ መልእክት አስቀምጦ፣ “ወደ ባላቅ ተመልሰህ ይህን መልእክት ንገረው” አለው።


እግዚአብሔር ያልረገመውን፣ እኔ እንዴት ረግማለሁ? እግዚአብሔር ያላወገዘውንስ፣ እንዴት አወግዛለሁ?


ከዚህ በኋላ በለዓም ተነሥቶ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ባላቅም መንገዱን ቀጠለ።


ይሁን እንጂ አምላክህ እግዚአብሔር በለዓምን አልሰማውም፤ አምላክህ እግዚአብሔር ስለሚወድድህ ርግማኑን በረከት አደረገልህ።


ኀይላቸው መድከሙን፣ ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው አለመቅረቱን በሚያይበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ለአገልጋዮቹም ይራራል።


እነርሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንደ ገና አለቀሱ፤ ከዚያም ዖርፋ ዐማቷን ስማ ተሰናበተቻት፤ ሩት ግን ልትለያት ስላልፈለገች ተጠመጠመችባት።


跟着我们:

广告


广告