Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 27:33 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 በዚህ ጊዜ ይሥሐቅ ክፉኛ እየተንቀጠቀጠ፣ “ታዲያ ቀደም ሲል ዐድኖ ያመጣልኝ ማን ነበር? አንተ ከመምጣትህ በፊት በልቼ መረቅሁት፤ እርሱም በርግጥ የተባረከ ይሆናል” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ይስሐቅም እጅግ ደነገጠ እንዲህም አለ፦ “ያደነውን አደን ወደ እኔ ያመጣ ማን ነው? አንተ ሳትመጣም ከሁሉ በላሁ ባረክሁትም፥ እርሱም የተባረከ ሆኖ ይኖራል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ይስሐቅም እጅግ ደንግጦ እየተንቀጠቀጠ “ታዲያ፥ አውሬ አድኖ ያመጣልኝ ማን ነበር? ልክ አንተ ከመምጣትህ በፊት ተመገብኩ፤ የመጨረሻ ምርቃቴንም ሰጠሁት፤ ምርቃቱም የእርሱ ሆኖ ይኖራል” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ይስ​ሐ​ቅም እጅግ ደነ​ገጠ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ያደ​ነ​ውን አደን ወደ እኔ ያመ​ጣው ማን ነው? አንተ ሳት​መ​ጣም ከሁሉ በላሁ፤ ባረ​ክ​ሁ​ትም፤ እር​ሱም የተ​ባ​ረከ ነው።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ይስሐቅም እጅግ ደነገጠ እንዲህም አለ፦ ያደነውን አደን ወደ እኔ ያመጣ ማን ነው? አንተ ሳትመጣም ከሁሉ በላሁ ባረክሁትም እርሱም የተባረከ ሆኖ ይኖራል።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 27:33
14 交叉引用  

እግዚአብሔርም እንዲህ አላት፤ “ሁለት ወገኖች በማሕፀንሽ አሉ፤ ሁለትም ሕዝቦች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንደኛው ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል” አላት።


ይሥሐቅም፣ “ወንድምህ መጥቶ አታልሎኝ ምርቃትህን ወስዶብሃል” አለው።


ይሥሐቅ ያዕቆብን አስጠርቶ ከመረቀው በኋላ፣ እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ምንም ቢሆን ከነዓናዊት ሴት አታግባ።


ስለዚህ ነገር ባሰብሁ ቍጥር እደነግጣለሁ፤ ሰውነቴም በፍርሀት ይንቀጠቀጣል።


“ልቤ በዚህ በኀይል ይመታል፤ ከስፍራውም ዘለል ዘለል ይላል።


ፍርሀትና እንቅጥቃጤ መጣብኝ፤ ሽብርም ዋጠኝ።


እባርክ ዘንድ ትእዛዝ ተቀብያለሁ፤ እርሱ ባርኳል፤ እኔም ልለውጠው አልችልም።


ሌባው ሊሰርቅ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ብቻ ይመጣል፤ እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ።


የእግዚአብሔር ስጦታና ጥሪ ጸጸት የለበትም።


በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤


ይሥሐቅ ወደ ፊት የሚሆነውን ዐስቦ ያዕቆብንና ዔሳውን በእምነት ባረካቸው።


跟着我们:

广告


广告