Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 27:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እናቱም፣ “ልጄ ሆይ፤ የአንተ ርግማን በእኔ ላይ ይድረስ፤ ግድ የለህም፤ እንደ ነገርሁህ ሄደህ ጠቦቶቹን አምጣልኝ” አለችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እናቱም አለችው፦ “ልጄ ሆይ፥ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን፥ ቃሌን ብቻ ስማኝ፥ ሂድና አምጣልኝ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እናቱም “ልጄ ሆይ፥ የአንተ ርግማን በእኔ ላይ ይሁን፤ አሁንም እንደ ነገርኩህ አድርግ፤ ሄደህ ጠቦቶቹን አምጣልኝ” አለችው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እና​ቱም አለ​ችው፥ “ልጄ ሆይ፥ መር​ገ​ምህ በእኔ ላይ ይሁን፥ ቃሌን ብቻ ስማኝ፤ ሂድና ያል​ሁ​ህን አም​ጣ​ልኝ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እናቱም አለችው፦ ልጄ ሆይ፥ መርገምህ በእኔ ላይ ይሁን ቃሌን ብቻ ስማኝ ሂድና አምጣልኝ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 27:13
12 交叉引用  

እግዚአብሔርም እንዲህ አላት፤ “ሁለት ወገኖች በማሕፀንሽ አሉ፤ ሁለትም ሕዝቦች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንደኛው ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል” አላት።


ያዕቆብም ዔሳውን፣ “እንግዲያማ፣ አስቀድመህ ማልልኝ” አለው፤ ስለዚህም ማለለት፤ ብኵርናውንም ለያዕቆብ ሸጠለት።


እርሱም ሄዶ ጠቦቶቹን ለእናቱ አመጣላት፤ እርሷም ልክ አባቱ እንደሚወድደው ዐይነት አጣፍጣ ጥሩ ምግብ አዘጋጀችለት።


አሁንም ልጄ ሆይ፤ እኔ የምልህን አድርግ፤ በካራን ምድር ወደሚኖረው ወደ ላባ ቶሎ ሽሽ።


ልጄ ሆይ፤ እንግዲህ የምነግርህን በጥሞና ስማኝ፤ የምልህንም አድርግ።


ስለ ልጁ ደኅንነት እኔ ራሴ ኀላፊ ነኝ፤ ስለ እርሱም በግል ተጠያቂ እሆናለሁ፤ እርሱንም በደኅና መልሼ ባላመጣውና እዚህ በፊትህ ባላቆመው ለዘላለም በደለኛው እኔ ልሁን።


ነገር ግን የቴቁሔዪቱም ሴት፣ “ንጉሥ ጌታዬ፣ በደሉ በእኔና በአባቴ ቤተ ሰብ ላይ ይሁን፤ ንጉሡና ዙፋኑ ከበደል የነጹ ይሁኑ” አለች።


እናቱ ክፋትን እንዲያደርግ ትመክረው ስለ ነበር፣ እርሱም በአክዓብ ቤት መንገድ ሄደ።


ሕዝቡም በሙሉ፣ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን!” ብለው መለሱ።


በእግሩም ላይ ወድቃ እንዲህ አለች፤ “ጌታዬ ሆይ፤ በደሉ በእኔ ላይ ብቻ ይሁን፤ እባክህ አገልጋይህ ታናግርህ፤ የምትልህንም ስማ።


跟着我们:

广告


广告