Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 26:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ይሥሐቅ ብዙ ጊዜ በዚያ ከኖረ በኋላ፣ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ አንድ ቀን ወደ ውጭ ሲመለከት፣ ይሥሐቅ ሚስቱን ርብቃን ሲዳራት አየ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በዚያም ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ በመስኮት ሆኖ ጎበኘ፥ ይስሐቅም ሚስቱን ርብቃን ሲዳራት አየ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ይስሐቅ እዚያ አገር ብዙ ጊዜ ከቈየ በኋላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቤሜሌክ በመስኮት ወደ ውጪ ሲመለከት ይስሐቅና ርብቃ እንደ ባልና ሚስት በመዳራት ሲጫወቱ አየ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በዚ​ያም ብዙ ቀን ተቀ​መጠ። የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ንጉሥ አቤ​ሜ​ሌ​ክም በመ​ስ​ኮት ሆኖ በተ​መ​ለ​ከተ ጊዜ ይስ​ሐ​ቅን ከሚ​ስቱ ከር​ብቃ ጋር ሲጫ​ወት አየው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በዚያም ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኍላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌም በመስኮት ሆኖ ጎበኘ፥ ይስሐቅም ሚስቱን ርብቃን ሲዳራት አየ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 26:8
8 交叉引用  

የዚያም አገር ሰዎች ስለ ሚስቱ በጠየቁት ጊዜ፣ “እኅቴ ናት” አለ፤ ምክንያቱም፣ “ሚስቴ ናት ብል ርብቃ ቈንጆ ስለ ሆነች፣ ያገሬው ሰዎች በርሷ ምክንያት ይገድሉኛል” በማለት ፈርቶ ነበር።


አቢሜሌክም ይሥሐቅን ጠርቶ፣ “እርሷ ሚስትህ ሆና ሳለች፣ እንዴት ‘እኅቴ ናት’ ትላለህ?” አለው። ይሥሐቅም፣ “በርሷ ሰበብ፣ ሕይወቴን እንዳላጣ ብዬ ነው” አለው።


በቤቴ መስኮት፣ በዐይነ ርግቡ ወደ ውጭ ተመለከትሁ።


አምላክ ከፀሓይ በታች በሰጠህ በዚህ ትርጕም የለሽ የሕይወት ዘመን ሁሉ፣ ከንቱ በሆኑትም ቀኖችህ ሁሉ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋራ ደስ ይበልህ፤ በሕይወትህና ከፀሓይ በታች በምትደክምበት ነገር ሁሉ ይህ ዕድል ፈንታህ ነውና።


ውዴ ሚዳቋ ወይም የዋሊያ ግልገል ይመስላል፤ እነሆ፤ ከቤታችን ግድግዳ ኋላ ቆሟል፤ በመስኮት ትክ ብሎ ወደ ውስጥ ያያል፤ በፍርግርጉም እያሾለከ ይመለከታል።


ጕልማሳ ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣ ልጆችሽ እንዲሁ ያገቡሻል፤ ሙሽራ በሙሽራዪቱ ደስ እንደሚለው፣ አምላክሽም በአንቺ ደስ ይለዋል።


“የሲሣራ እናት በመስኮት ተመለከተች፤ በዐይነ ርግቡ ቀዳዳም ጮኻ ተጣራች፤ ‘ለምን ሠረገላው ሳይመጣ ዘገየ? የሠረገሎቹስ ድምፅ ለምን ጠፋ?’ አለች።


跟着我们:

广告


广告