ዘፍጥረት 26:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም20 የጌራራ እረኞች ግን፣ “ውሃው የእኛ ነው” በማለት ከይሥሐቅ እረኞች ጋራ ጠብ አነሡ፤ ከዚህ የተነሣ ይሥሐቅ ያን የውሃ ጕድጓድ ኤሴቅ ብሎ ጠራው፤ በጕድጓዱ ምክንያት ተጣልተውታልና። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 የጌራራ አገር እረኞች ከይስሐቅ እረኞች ጋር፦ “ውኃው የእኛ ነው” ሲሉ ተከራከሩ፥ የዚያችንም ጉድጓድ ስም “ኤሴቅ” ብሎ ጠራት፥ ለእርሷ ሲሉ ተጣልተዋልና። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 የገራር እረኞች ግን “ይህ ውሃ የእኛ ነው” በማለት ከይስሐቅ እረኞች ጋር ተጣሉ። በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ጒድጓዱን “ዔሤቅ” ብሎ ሰየመው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 የጌራራ እረኞች ከይስሐቅ እረኞች ጋር፥ “ውኃው የእኛ ነው” ሲሉ ተጣሉ፤ የዚያችንም ጕድጓድ ስም “ዐዘቅተ ዐመፃ” ብሎ ጠራት፤ እነርሱ በድለውታልና። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 የጌራራ አገር እረኞች ለይስሐቅ እረኞች ጋር፦ ውኃው የእኛ ነው ሲሉ ተከራከሩ፤ የዚይችንም ጕድጓድ ስም ኤሴቅ ብሎ ጠራት ለእርስዋ ሲሉ ተጣልተዋልና። 参见章节 |