Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 16:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አብራምም፣ “አገልጋይሽ እንደ ሆነች በእጅሽ ውስጥ ናት፤ የፈለግሽውን አድርጊባት” አላት። ከዚያም ሦራ ስላሠቃየቻት አጋር ጥላት ኰበለለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አብራምም ሣራን፦ እነሆ ባርያሽ በእጅሽ ናት፥ እንደ ወደድሽ አድርጊባት አላት። ሦራም ባሠቀየቻት ጊዜ አጋር ከፊትዋ ኮበለለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አብራምም “መልካም ነው፤ እርስዋ የአንቺ አገልጋይ ስለ ሆነች በቊጥጥርሽ ሥር ናት፤ የፈለግሺውን ነገር አድርጊ” አላት። ከዚህ በኋላ ሣራይ አጋርን እጅግ ስላሠቃየቻት አጋር ከቤት ወጥታ ኰበለለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አብ​ራ​ምም ሚስ​ቱን ሦራን፥ “እነሆ፥ አገ​ል​ጋ​ይሽ በእ​ጅሽ ናት፤ እንደ ወደ​ድሽ አድ​ር​ጊ​ባት” አላት። ሦራም አጋ​ርን አሠ​ቃ​የ​ቻት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ኰበ​ለ​ለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አብራምም ሦራን፥ እነሆ ባሪያሽ በእጅሽ ናት፤ እንደ ወደድሽ አድርጊባት አላት። ሦርም ባሠቀየቻት ጊዜ አጋር ከፊትዋ ኮበለለች።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 16:6
15 交叉引用  

የእግዚአብሔርም መልአክ፣ “ወደ እመቤትሽ ተመለሽ፤ ለርሷም ተገዥላት” አላት።


አገልጋዩም ከጌታው ግመሎች መካከል ዐሥሩን ወሰደ፤ ምርጥ ምርጡንም ዕቃ ሁሉ ጭኖ፣ የናኮር ከተማ ወደምትገኝበት ወደ ሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ተጓዘ።


እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “እነሆ፤ እርሱ በእጅህ ነው፤ ሕይወቱን ግን እንዳትነካ” አለው።


ፈርዖንም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ፤ ሙሴ ግን ከፈርዖን ሸሽቶ ወደ ምድያም ሄደ፤ እዚያም እንደ ደረሰ በአንድ የውሃ ጕድጓድ አጠገብ ተቀመጠ።


ታጋሽ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ ግልፍተኛ ሰው ግን ቂልነትን ያሳያል።


የለዘበ መልስ ቍጣን ያበርዳል፤ ክፉ ቃል ግን ቍጣን ይጭራል።


ከቤቱ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣ ጐጆዋን ለቅቃ እንደምትባዝን ወፍ ነው።


አገልጋይ በቃል ብቻ ሊታረም አይችልም፤ ቢያስተውለውም እንኳ በጀ አይልም።


የገዥ ቍጣ በተነሣብህ ጊዜ፣ ስፍራህን አትልቀቅ፤ ትዕግሥት ታላቁን ጥፋት ጸጥ ያደርጋልና።


ንጉሡ ሴዴቅያስም፤ “እርሱ በእጃችሁ ነው፤ ንጉሡ እናንተን ተቃውሞ ምንም ማድረግ አይችልም” አለ።


እነሆ፤ አሁን በእጅህ ውስጥ ነን፤ በጎና ትክክል መስሎ የታየህን ነገር ሁሉ አድርግብን።”


ባሎች ሆይ፤ እናንተም ደግሞ ጸሎታችሁ እንዳይደናቀፍ በኑሯችሁ ሁሉ ለሚስቶቻችሁ ዐስቡላቸው፤ ደካሞች ስለ ሆኑና የሕይወትንም በረከት ዐብረዋችሁ ስለሚወርሱ አክብሯቸው።


跟着我们:

广告


广告