Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 10:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የሴም ልጆች፦ ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ እና አራም ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድና አራም ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የሴ​ምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አር​ፋ​ክ​ስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ቃይ​ናን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የሴምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም ናቸው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 10:22
19 交叉引用  

ለያፌት ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅደመ አያት ነው።


የሴም ትውልድ ይህ ነው፦ ሁለት ዓመት ከጥፋት ውሃ በኋላ ሴም በ100 ዓመቱ አርፋክስድን ወለደ።


ደግሞም፤ “የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፤ ከነዓንም የሴም ባሪያ ይሁን።


ከዚያም የአሦር ንጉሥ ፎሓ ምድሪቱን ወረረ፤ ምናሔም ርዳታውን ለማግኘትና በመንግሥቱ ላይ ያለውን ይዞታ ለማጽናት ሲል፣ አንድ ሺሕ መክሊት ብር ሰጠው።


እርሱም እየተናገረ ሳለ፣ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፣ “ከለዳውያን በሦስት ቡድን መጥተው ጥቃት አደረሱ፤ ግመሎችህንም ይዘው ሄዱ፤ አገልጋዮቹን በሰይፍ ገደሉ፤ እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ” አለው።


በዚያ ቀን፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደ ገና የተረፈውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦር፣ ከግብጽ፣ ከጳትሮስ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኤላም፣ ከባቢሎን፣ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።


የሚያስጨንቅ ራእይ አየሁ፤ ከሓዲ አሳልፎ ይሰጣል፤ ዘራፊ ይዘርፋል። ኤላም ሆይ፤ ተነሺ፤ ሜዶን ሆይ፤ ክበቢ፤ እርሷ ያደረሰችውን ሥቃይ ሁሉ አስቀራለሁ።


ኤላም የፍላጻ ሰገባ፣ ፈረሷንና ሠረገላዋን አዘጋጀች፤ ቂርም ጋሻዋን አነገበች።


“በመካከላቸው ምልክት አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም የተረፉትን አንዳንዶቹን ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፣ ወደ ፉጥ፣ ወደ ታወቁት ቀስተኞች ወደ ሉድ፣ ወደ ቶቤልና ያዋን እንዲሁም ዝናዬን ወዳልሰሙትና ክብሬን ወዳላዩት ራቅ ወዳሉት ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በሕዝቦችም መካከል ክብሬን ይናገራሉ።


የዘምሪ፣ የኤላምና የሜዶን ነገሥታትን ሁሉ፣


“ኤላም በዚያ አለች፤ ሰራዊቷም ሁሉ በመቃብሯ ዙሪያ አለ፤ ሁሉም ታርደዋል፤ በሰይፍ ወድቀዋል። በሕያዋን ምድር ሽብር የነዙ ሁሉ ሳይገረዙ ከምድር በታች ወርደዋል፤ ወደ ጕድጓድ ከወረዱት ጋራ ዕፍረታቸውን ተሸክመዋል፤


በራእዩም፣ በኤላም አውራጃ በሱሳ ግንብ ራሴን አየሁት፤ በራእዩም በኡባል ወንዝ አጠገብ ነበርሁ።


ከዚያም በለዓም ንግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ፤ “ባላቅ ከአራም አመጣኝ፣ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች። ‘ና ያዕቆብን ርገምልኝ፤ መጥተህም እስራኤልን አውግዝልኝ’ አለኝ።


ያም ሆኖ ግን እናንተ ቄናውያን፤ አሦር በምርኮ ሲወስዳችሁ ትደመሰሳላችሁ።”


የቃይንም ልጅ፣ የአርፋክስድ ልጅ፣ የሴም ልጅ፣ የኖኅ ልጅ፣ የላሜህ ልጅ፣


እኛ የጳርቴና፣ የሜድ፣ የኢላሜጤም ሰዎች፣ በመስጴጦምያ፣ በይሁዳ፣ በቀጰዶቅያ፣ በጳንጦስ፣ በእስያ፣


跟着我们:

广告


广告