Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ገላትያ 4:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እነዚያ ሰዎች ወደ ራሳቸው ሊወስዷችሁ ይተጋሉ፤ ለበጎ ግን አይደለም፤ የሚፈልጉት እናንተን ከእኛ ነጥለው የራሳቸው ሊያደርጓችሁ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ይቀኑባችኋል፥ ለመልካም ግን አይደለም፤ ነገር ግን እናንተ በእነርሱ ላይ እንድትቀኑ ሊያስቀሩአችሁ ይወዳሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ሌሎች ሰዎች ስለ እናንተ በመጨነቅ ያስባሉ፤ ይሁን እንጂ ይህን የሚያደርጉት ለመልካም አይደለም፤ የእነርሱ ፍላጎት እናንተ ከእኛ እንድትለዩና ለእነርሱ በትጋት እንድታስቡ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እነ​ዚ​ያማ ይቀ​ኑ​ባ​ች​ኋል፤ ነገር ግን በእ​ነ​ርሱ ላይ እን​ድ​ት​ቀኑ ሊዘ​ጉ​አ​ችሁ ይወ​ዳሉ እንጂ ለመ​ል​ካም አይ​ደ​ለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 በብርቱ ይፈልጉአችኋል፥ ለመልካም አይደለም ነገር ግን በብርቱ ትፈልጉአቸው ዘንድ በውጭ ሊያስቀሩአችሁ ይወዳሉ።

参见章节 复制




ገላትያ 4:17
14 交叉引用  

“እናንተ ግብዞች የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን፤ አንድን ሰው ወደ አይሁድ ሃይማኖት ለማስገባት በባሕርና በየብስ ስለምትጓዙ፣ ባመነም ጊዜ ከእናንተ በዕጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት ወዮላችሁ።


ለእግዚአብሔር ቀናተኞች እንደ ሆኑ ስለ እነርሱ መመስከር እችላለሁና፤ ቅናታቸው ግን ከዕውቀት የተነሣ አይደለም።


እንደ እነዚህ ያሉት ሰዎች የሚያገለግሉት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን የራሳቸውን ሆድ ነው። በለሰለሰ አንደበታቸውና በሽንገላ የዋሆችን ያታልላሉ።


በሁሉም ነገር ስለምታስቡልኝና ከእኔ የተቀበላችሁትን ትምህርት አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።


ከእናንተ አንዳንዶቹ ወደ እናንተ የማልመጣ መስሏቸው ታብየዋል፤


አሁንስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝታችኋል! ሀብታምም ሆናችኋል! ከእኛም ተለይታችሁ ነግሣችኋል! በርግጥ ብትነግሡማ እኛም ከእናንተ ጋራ በነገሥን ነበር፤


ነገር ግን እባብ ሔዋንን በተንኰል እንዳሳታት ምናልባት የእናንተም ልቡና ተበላሽቶ ለክርስቶስ ካላችሁ ቅንነትና ንጽሕና እንዳትወሰዱ እሠጋለሁ።


እውነቱን ስለ ነገርኋችሁ ጠላት ሆንሁባችሁን?


ለበጎ እስከ ሆነ ድረስ ተቈርቋሪ መሆን መልካም ነው፤ ይህም መሆን የሚገባው ዘወትር እንጂ እኔ ከእናንተ ጋራ ሳለሁ ብቻ አይደለም።


ሁሉም የኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟላት ይሯሯጣሉና።


ከንቱ ቃል እየደረደሩ በስሕተት ከሚኖሩት መካከል አምልጠው የመጡትን ሰዎች በሴሰኛ ሥጋዊ ምኞት በማባበል ያታልላሉና።


እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን እየተስገበገቡ በፈጠራ ታሪካቸው ይበዘብዟችኋል። ፍርዳቸው ከጥንት ጀምሮ ዝግጁ ነው፤ መጥፊያቸውም አያንቀላፋም።


跟着我们:

广告


广告