Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 8:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በተጨማሪም ዳዊትና ሹማምቱ ሌዋውያኑን እንዲረዳ ካቋቋሙት ከቤተ መቅደሱ አገልጋዮች ቡድን 220 አመጡ፤ እነዚህም ሁሉ በየስማቸው ተመዘገቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ዳዊትና ባለሥልጣኖቹ ሌዋውያንን እንዲያገለግሉ ከመረጧቸው የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ውስጥ ሁለት መቶ ሀያ የቤተ መቅደስ አገልጋዮችን አመጡ፤ እነዚህም ሁሉ በየሥማቸው ተጠቅሰዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በተጨማሪም የቀድሞ አባቶቻቸው ሌዋውያንን ይረዱ ዘንድ በንጉሥ ዳዊትና በባለሟሎቹ ተሹመው የነበሩ ብዛታቸው ሁለት መቶ ኻያ የሆነ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ነበሩ፤ እነርሱም በየስማቸው ተመዝግበዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ዳዊ​ትና አለ​ቆቹ ከሰ​ጡ​አ​ቸው ናታ​ኒም ውስጥ ሁለት መቶ ሃያ ናታ​ኒ​ምን አመጡ፤ እነ​ዚ​ህም ሁሉ በስም በስ​ማ​ቸው ተሰ​በ​ሰቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሌዋውያንንም እንዲያገለግሉ ዳዊትና አለቆቹ ከሰጡአቸው ናታኒም ውስጥ ሁለት መቶ ሀያ ናታኒም አመጡ፤ እነዚህም ሁሉ በስም በስማቸው ተጠሩ።

参见章节 复制




ዕዝራ 8:20
7 交叉引用  

በመጀመሪያ በየርስታቸውና በየከተሞቻቸው ተመልሰው የሰፈሩት ጥቂት እስራኤላውያን፣ ካህናት፣ ሌዋውያንና በቤተ መቅደሱ ውስጥ የጕልበት ሥራ የሚሠሩ አገልጋዮች ነበሩ።


የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፦ የሲሐ፣ የሐሡፋ የጠብዖት ዘሮች፤


እንደዚሁም አንዳንድ እስራኤላውያን፣ ከካህናት፣ ከሌዋውያን፣ ከመዘምራን፣ ከበር ጠባቂዎችና ከቤተ መቅደሱ አገልጋዮች ጋራ በመሆን በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት በሰባተኛው ዓመት ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።


እነርሱንም ካሲፍያ በሚባል ስፍራ አለቃ ወደ ሆነው ወደ አዶ ላክኋቸው፤ በአምላካችን ቤት የሚያገለግሉ ሰዎችን ያመጡልን ዘንድ በካሲፍያ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ለሆኑት ለአዶና ለሥጋ ዘመዶቹ የሚናገሩትን አስታወቅኋቸው።


እንዲሁም ሐሸቢያንና ከሜራሪ ዘሮች የሻያን፣ ከወንድሞቹና ከአጎቶቹ ወንዶች ልጆች ጋራ 20 ወንዶችን አመጡልን።


ሌዋውያኑን ለአሮንና ለልጆቹ ስጥ፤ እነርሱም ከእስራኤላውያን ተለይተው ለርሱ ፈጽመው የተሰጡ ናቸው።


አዎን፤ አንተ ታማኝ ባልደረባዬ ሆይ፤ ወንጌልን በማሠራጨት ረገድ ከእኔና ከቀሌምንጦስ ጋራ እንዲሁም ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎች የሥራ ጓደኞቼ ጋራ የተጋደሉትን እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ።


跟着我们:

广告


广告