Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 7:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ለአምላክህ ሕግና ለንጉሡ ሕግ የማይታዘዝ ማንኛውም ሰው፣ የሞት ወይም የስደት ወይም የንብረት መወረስ ወይም የእስራት ቅጣት ይፈጸምበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 የአምላክህን ሕግና የንጉሡን ትእዛዝ በማያደርግ በማንም ላይ ሞት ወይም ስደት ወይም ንብረት መወረስ ወይም ግዞት በፅኑ ይፈረድበት።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ለእግዚአብሔር ሕግ ወይም ለመንግሥት ሕግ ሁሉ የማይታዘዝ ማንም ሰው ቢኖር በጥንቃቄ እየተመረመረ በሞት ወይም ከሀገር በመባረር ወይም ሀብት ንብረቱን በመወረስ ወይም በእስራት ይቀጣ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ሕግ፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ሕግ በማ​ያ​ደ​ርግ ሁሉ ላይ ሞት፥ ወይም ስደት፥ ወይም ገን​ዘብ መወ​ረስ፥ ወይም ግዞት በፍ​ጥ​ነት ይፈ​ረ​ድ​በት።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 የአምላክህንም ሕግ፥ የንጉሡንም ሕግ በማያደርግ ሁሉ ላይ ሞት ወይም ስደት ወይም ገንዘብን መወረስ ወይም ግዞት በፍጥነት ይፈረድበት።”

参见章节 复制




ዕዝራ 7:26
12 交叉引用  

እንዲሁም ንጉሡና ሹማምቱ በእግዚአብሔር ቃል መሠረት ያዘዙትን እንዲፈጽሙ አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በይሁዳ ላይ ነበር።


ዕዝራ፣ ነገሩ በእጅህ ነው፤ ተነሥ! እኛም እንደግፍሃለን፤ በርትተህም አድርገው።”


ዐዋጁም በሦስት ቀን ውስጥ ያልመጣ ማንም ሰው በሹማምቱና በሽማግሌዎቹ ውሳኔ መሠረት ንብረቱ ሁሉ እንዲወረስ፣ ራሱም ከምርኮኞቹ ጉባኤ እንዲወገድ የሚያዝ ነበር።


ደግሞም ይህን ትእዛዝ የሚለውጥ ማንም ሰው ቢኖር፣ ከቤቱ ምሰሶ ተነቅሎ በምሰሶው ላይ እንዲሰቀል፣ ስለ ወንጀሉም ቤቱ የቈሻሻ መጣያ እንዲሆን አዝዣለሁ።


ይህን ትእዛዝ ለማፍረስ ወይም በኢየሩሳሌም የሚገኘውን ቤተ መቅደስ ለማጥፋት እጁን የሚያነሣ ማንኛውንም ንጉሥ ወይም ሕዝብ፣ ስሙን በዚያ እንዲኖር ያደረገ አምላክ ያጥፋው። እኔ ዳርዮስ በትጋት እንዲፈጸም ይህን ትእዛዝ ሰጥቻለሁ።


እግዚአብሔር ግን ለዘላለም ያንኰታኵትሃል፤ ይነጥቅሃል፤ ከድንኳንህም መንጥቆ ያወጣሃል፤ ከሕያዋንም ምድር ይነቅልሃል። ሴላ


“በማንኛውም የመንግሥቴ ግዛት ሰው ሁሉ፣ የዳንኤልን አምላክ እንዲፈራና እንዲያከብር ይህን ዐዋጅ አውጥቻለሁ። “እርሱ ለዘላለም የሚኖር፣ ሕያው አምላክ ነውና፣ መንግሥቱ አይጠፋም፤ ለግዛቱም መጨረሻ የለውም።


“የዚህን ሕግ ቃሎች በመፈጸም የማይጸና የተረገመ ይሁን።” ሕዝቡም ሁሉ፣ “አሜን!” ይበል።


跟着我们:

广告


广告