Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 6:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ስለዚህ ከምርኮ የተመለሱት እስራኤላውያን የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በአምልኮ ይፈልጉት ዘንድ ራሳቸውን ከአረማውያን ጎረቤቶቻቸው ርኩሰት ከለዩት ሁሉ ጋራ በሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ከምርኮ የተመለሱት የእስራኤል ልጆች፥ የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመፈለግ ራሳቸውን ከምድር አሕዛብ ርኩሰት ለይተው ወደ እነርሱ መጥተው የነበሩት ሁሉ በሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 መሥዋዕቱንም ሁሉ ከምርኮ የተመለሱት እስራኤላውያን እንዲሁም በዚያች ምድር የሚኖሩትን የአሕዛብን ሥርዓት ትተው የነበረውን ልማድ ትተው የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ሁሉ እንዲመገቡት ተደረገ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ከም​ር​ኮም ተመ​ል​ሰው የመ​ጡት የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልጉ ዘንድ ራሳ​ቸ​ውን ከም​ድር አሕ​ዛብ ርኵ​ሰት ለይ​ተው ወደ እነ​ርሱ መጥ​ተው የነ​በ​ሩት ሁሉ ፋሲ​ካ​ውን በሉ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ከምርኮም ተመልሰው የመጡት የእስራኤል ልጆች፥ የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ ራሳቸውን ከምድር አሕዛብ ርኵሰት ለይተው ወደ እነርሱ መጥተው የነበሩት ሁሉ በሉ፤

参见章节 复制




ዕዝራ 6:21
13 交叉引用  

ምንም እንኳ በመቅደሱ ሥርዐት መሠረት የነጹ ሆነው ባይገኙም፣ የአባቶቻቸው አምላክ የሆነውን እግዚአብሔር አምላካቸውን ለመፈለግ ልባቸውን የሚያዘጋጁትን ሁሉ ይቅር በላቸው።”


እነዚህ ነገሮች ከተፈጸሙ በኋላ መሪዎቹ ወደ እኔ መጥተው እንዲህ አሉኝ፤ “ካህናቱንና ሌዋውያኑን ጨምሮ የእስራኤል ሕዝብ ከጎረቤቶቻቸው ከከነዓናውያን፣ ከኬጢያውያን፣ ከፌርዛውያን፣ ከኢያቡሳውያን፣ ከአሞናውያን፣ ከሞዓባውያን፣ ከግብጻውያንና ከአሞራውያን ርኩሰት ራሳቸውን አልለዩም።


ያቃለልነውም በባሮችህ በነቢያት አማካይነት፣ ‘ለመውረስ የምትገቡባት ምድር በሕዝቦቿ ርኩሰት ተበክላለች፤ ከዳር እስከ ዳርም በአስጸያፊ ድርጊታቸውና በርኩሰታቸው ተሞልታለች፤


“የቀሩት ሕዝብ፦ ማለት ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑ፣ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ስለ እግዚአብሔር ሕግ ብለው ራሳቸውን ከጎረቤት አሕዛብ የለዩ ሁሉ፣ ሚስቶቻቸው፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው፣ የሚያውቁና የሚያስተውሉ ሁሉ ቃለ መሐላ ፈጸሙ፤


የእስራኤላውያን ዘር የሆኑትም ራሳቸውን ከባዕዳን ሁሉ ለዩ። ቆመውም ኀጢአታቸውንና የአባቶቻቸውን በደል ተናዘዙ።


ምስክርነትህ የጸና ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እስከ ዘላለሙ፣ ቤትህ በቅድስና ይዋባል።


እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ፣ ተለዩ! ተለዩ! ከመካከልዋ ውጡ፤ ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ ከዚያ ውጡ ንጹሓንም ሁኑ፤


ንጹሕ ውሃ እረጫችኋለሁ፤ እናንተም ንጹሕ ትሆናላችሁ፤ ከርኩሰታችሁ ሁሉና ከጣዖታቶቻችሁ ሁሉ አነጻችኋለሁ።


“ስለዚህ ከመካከላቸው ውጡ፤ ተለዩም፤ ይላል ጌታ። ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ።”


እንግዲህ፣ ወዳጆች ሆይ፤ ይህ የተስፋ ቃል ስላለን፣ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርገው።


跟着我们:

广告


广告