Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 4:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እኔም ትእዛዝ ሰጥቼ ምርመራ ተደርጓል፤ በምርመራውም መሠረት ይህች ከተማ ከጥንት ጀምሮ በነገሥታት ላይ ስታምፅ የኖረች የዐመፅና የወንጀል መናኸሪያ እንደ ሆነች ማስረጃ ተገኝቷል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እኔም አዝዣለሁ፥ ተመረመረም፥ ይህችም ከተማ ከጥንት ጀምራ በነገሥታት ላይ ዓመፀኛ እንደ ነበረች፥ በእርሷም ዓመፅና ሽፍትነት እንደ ተደረገ ተገኘ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በእርሱም መነሻነት ጥብቅ ምርምርና ጥናት እንዲደረግ ትእዛዝ ሰጥቻለሁ፤ ከጥናቱም የተገኘው ውጤት ኢየሩሳሌም ከጥንት ጀምሮ በመንግሥት ሥልጣን ላይ ስታምፅ የኖረች ዐመፀኞችና አስቸጋሪዎች ሰዎች የሞሉባት ከተማ እንደ ነበረች ያስረዳል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እኔም አዝ​ዣ​ለሁ፤ ተመ​ረ​መ​ረም፤ ይህ​ችም ከተማ ከጥ​ንት ጀምራ በነ​ገ​ሥ​ታት ላይ ዐመ​ፀኛ እንደ ነበ​ረች፥ በእ​ር​ስ​ዋም ዐመ​ፅና ሽፍ​ት​ነት እንደ ተደ​ረገ ተገኘ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እኔም አዝዣለሁ፤ ተመረመረም፤ ይህችም ከተማ ከጥንት ጀምራ በነገሥታት ላይ ዓመፀኛ እንደ ነበረች፥ በእርስዋም ዓመፅና ሽፍትነት እንደ ተደረገ ተገኘ።

参见章节 复制




ዕዝራ 4:19
10 交叉引用  

እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ ስለ ነበር የሚያደርገው ሁሉ ተከናወነለት። በአሦር ንጉሥ ላይ ዐመፀ፤ ግብር መገበሩንም ተወ።


እንግዲህ ይህ ሁሉ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሊደርስ የቻለው ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ነበር፤ በመጨረሻም ከፊቱ አስወገዳቸው። በዚህ ጊዜ ሴዴቅያስ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።


ስለዚህ በአባቶችህ ቤተ መዛግብት ምርመራ ይደረግ፤ በእነዚህ መዛግብት ውስጥ ይህች ከተማ ዐመፀኛ ከተማ እንደ ሆነች፣ ነገሥታትንና አውራጃዎችን የጐዳችና ከጥንት ጀምሮ የዐመፅ ጐሬ ስለ መሆኗ ማስረጃ ታገኛለህ፤ እንግዲህ ከተማዪቱ የተደመሰሰችው በዚህ ምክንያት ነው።


የላካችሁልኝ ደብዳቤ በፊቴ ተተርጕሞ ተነብቧል።


ኢየሩሳሌም ከኤፍራጥስ ማዶ ያለውን አገር ሁሉ የገዙ፣ ቀረጥ፣ ግብርና እጅ መንሻም ይቀበሉ የነበሩ ኀያላን ነገሥታት ነበሯት።


አሁንም ንጉሡን ደስ የሚያሠኘው ቢሆን፣ ይህ የእግዚአብሔር ቤት በኢየሩሳሌም እንዲሠራ ንጉሥ ቂሮስ በርግጥ ትእዛዝ ሰጥቶ እንደ ሆነ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ግምጃ ቤት የተቀመጡት መዛግብት እንዲመረመሩ ያድርግ፤ ከዚያም ንጉሡ ስለዚህ ጕዳይ የወሰነውን ይላክልን።


ነገርን መሰወር ለእግዚአብሔር ክብሩ ነው፤ ነገርን ፈልፍሎ ማውጣት ግን ለነገሥታት ክብራቸው ነው።


ጕዳዩን አጣራ፤ መርምር፤ በሚገባም ተከታተል፤ ነገሩ እውነት ሆኖ ከተገኘና ይህ አስጸያፊ ነገር በመካከልህ መፈጸሙ ከተረጋገጠ፣


跟着我们:

广告


广告