Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 4:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ደግሞም ታላቁና ኀያሉ አስናፈር አፍልሶ በሰማርያ ከተማና ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ እንዲሰፍሩ ካደረጋቸው ሌሎች ሕዝቦች ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ታላቁና የተከበረው አስናፋር ያፈለሳቸው በሰማርያና በወንዝ ማዶ ያኖራቸው የቀሩትም አሕዛብ ደብዳቤውን ጻፉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ታላቁና ኀያሉ ንጉሠ ነገሥት አሰናፈር ከየተወለዱበት አገር በማዛወር በሰማርያ ከተማና ከኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል በየአውራጃው እንዲሰፍሩ ካደረጋቸው ከሌሎችም ሕዝቦች ጋር በመተባበር የተጻፈ ሲሆን።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ታላ​ቁና ኀይ​ለ​ኛው አስ​ና​ፍር ያፈ​ለ​ሳ​ቸው፥ በሰ​ማ​ር​ያና በወ​ንዝ ማዶ ያኖ​ራ​ቸው፥ የቀ​ሩ​ትም አሕ​ዛብ ደብ​ዳ​ቤ​ውን ጻፉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ታላቁና ኃይለኛው አስናፈር ያፈለሳቸው፥ በሰማርያና በወንዝ ማዶ ያኖራቸው እና የቀሩትም አሕዛብ ደብዳቤውን ጻፉ።

参见章节 复制




ዕዝራ 4:10
8 交叉引用  

የይሁዳና የብንያም ጠላቶች ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በመሥራት ላይ መሆናቸውን ሲሰሙ፣


የላኩለት ደብዳቤ ቅጅ ይህ ነው፤ ለንጉሥ አርጤክስስ፣ በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ከሚኖሩት አገልጋዮችህ የተላከ፤


ንጉሡም ይህን መልስ ላከ፤ ለአገረ ገዥው ሬሁም፣ ለጸሓፊው ሲምሳይ፣ በሰማርያና በኤፍራጥስ ማዶ ለሚኖሩ ተባባሪዎቻቸው፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን፤


ከንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ፤ ለሰማይ አምላክ ሕግ መምህር ለሆነው ለካህኑ ለዕዝራ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን፤


በተባባሪዎቹና በሰማርያ ሰራዊት ፊት፣ “እነዚህ ደካማ አይሁድ ምን እያደረጉ ነው? ቅጥራቸውን መልሰው ሊሠሩ ነውን? መሥዋዕት ሊያቀርቡ ነውን? በአንዲት ጀንበር ሠርተው ሊጨርሱ ነውን? እንደዚያ ተቃጥሎ የፍርስራሽ ክምር የሆነውን ድንጋይ ነፍስ ሊዘሩበት ይችላሉን?” አለ።


“አሁንም አምላካችን ሆይ፤ ቃል ኪዳንህንና ዘላለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ ታላቅ፣ ኀያልና የተፈራህ አምላክ ሆይ፤ ከአሦር ነገሥታት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ፣ በነገሥታታችንና በመሪዎቻችን፣ በካህናታችንና በነቢያታችን፣ በአባቶቻችንና በመላው ሕዝብህ ላይ የደረሰው ይህ ሁሉ መከራ በፊትህ እንደ ቀላል ነገር አይታይ።


ለእያንዳንዱ የሚገባውን ስጡ፤ ግብር ከሆነ ግብርን፣ ቀረጥ ከሆነም ቀረጥን፣ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ ክብር ለሚገባውም ክብርን ስጡ።


跟着我们:

广告


广告