Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕዝራ 10:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ከዚያም ምርኮኞቹ ሁሉ በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ዐዋጅ ተነገረ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ምርኮኞቹ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አዋጅ ነገሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ከምርኮ የተመለሱትም ሁሉ በኢየሩሳሌም ይሰበሰቡ ዘንድ በመላው ኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምድር ሁሉ ታወጀ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የም​ርኮ ልጆች ሁሉም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ይሰ​በ​ሰቡ ዘንድ ወደ ይሁ​ዳና ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ዐዋጅ ነገረ

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7-8 ምርኮኞቹም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ፥ እንደ አለቆቹና እንደ ሽማግሌዎችም ምክር በሦስት ቀን ውስጥ ያልመጣ ሁሉ ንብረቱ ሁሉ እንዲወረስ፥ እርሱም ከምርኮው ጉባኤ እንዲለይ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አዋጅ ነገሩ።

参见章节 复制




ዕዝራ 10:7
4 交叉引用  

ስለዚህ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ፋሲካ ለማክበር ሕዝቡ ከመላው ኢየሩሳሌም እንዲመጣ፣ ከቤርሳቤህ እስከ ዳን ድረስ ዐዋጅ እንዲነገር ወሰኑ፤ በተጻፈው መሠረት በዓሉ ብዛት ባለው ሕዝብ ተከብሮ አያውቅም ነበርና።


በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ ዘመነ መንግሥት በመጀመሪያ ዓመት፣ በኤርምያስ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይፈጸም ዘንድ በግዛቱ ሁሉ ዐዋጅ እንዲያስነግርና ይህም እንዲጻፍ እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አነሣሣ፤ እርሱም እንዲህ አለ፤


ከዚያም ዕዝራ ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ተነሥቶ ወደ ኤልያሴብ ልጅ ወደ ዮሐናን ክፍል ገባ፤ ምርኮኞቹ ታማኝነታቸውን ከማጕደላቸው የተነሣ ያለቅስ ነበር፤ በዚያም ምግብ አልቀመሰም፤ ውሃም አልጠጣም።


ዐዋጁም በሦስት ቀን ውስጥ ያልመጣ ማንም ሰው በሹማምቱና በሽማግሌዎቹ ውሳኔ መሠረት ንብረቱ ሁሉ እንዲወረስ፣ ራሱም ከምርኮኞቹ ጉባኤ እንዲወገድ የሚያዝ ነበር።


跟着我们:

广告


广告