Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 8:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እኔም አየሁ፤ እነሆ፤ የሰውን ልጅ የሚመስል ነበረ፤ ወገቡ ከሚመስለው ጀምሮ ወደ ታች እንደ እሳት ያለ ነበር፤ ወገቡንም ከሚመስለው ጀምሮ ወደ ላይ እንደ ጋለ ብረት ያበራ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እኔም አየሁ፥ እነሆም ሰውን የሚመስል ነበረ፥ ወገቡ ከሚመስለው በታች እሳት፥ ከወገቡም በላይ እንደ ብርሃን የሚመስል፥ የሚያንጸባርቅ ነገር የሚመስል ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ቀና ብዬ ስመለከት መልኩ እንደ እሳት ነበልባል የሚያበራ የሰው አምሳያ አየሁ፤ ያም የሰው አምሳያ ከወገቡ በታች እሳት፥ ከወገቡ በላይ የሚያንጸባርቅ የጋለ ብረት ይመስል ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ከወ​ገቡ በታች እንደ እሳት የሚ​መ​ስል የሰው አም​ሳያ ነበረ፤ ከወ​ገ​ቡም ወደ ላይ እንደ ፀዳል ምሳሌ፥ እን​ደ​ሚ​ያ​ን​ጸ​ባ​ርቅ አይ​ነት ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ እንደ እሳት የሚመስል አምሳያ ነበረ፥ ከወገቡም ምሳሌ ወደ ታች እሳት ነበረ፥ ከወገቡም ምሳሌ ወደ ታች እሳት ነበረ፥ ከወገቡም ወደ ላይ እንደ ፀዳል ምሳሌ፥ እንደሚብለጨለጭም የወርቅ ምሳሌ ነበረ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 8:2
7 交叉引用  

እኔም አየሁ፤ ስመለከትም፣ እነሆ ዐውሎ ነፋስ ከሰሜን በኩል መጣ፤ ይኸውም በታላቅ ብርሃን የተከበበ፣ መብረቅን የሚረጭ ታላቅ ደመና ነበረ፤ የእሳቱም መኻል የጋለ ብረት ይመስል ነበር።


ወደዚያ ወሰደኝ፤ እነሆ መልኩ ናስ የሚመስል ሰው አየሁ፤ እርሱም የሐር ገመድና መለኪያ ዘንግ በእጁ ይዞ በመግቢያው በር ላይ ቆሞ ነበር።


በስድስተኛው ዓመት፣ በስድስተኛው ወር፣ በዐምስተኛው ቀን በቤቴ ተቀምጬ ሳለሁ፣ የይሁዳም ሽማግሌዎች በፊቴ ተቀምጠው ሳሉ፣ በዚያ የጌታ እግዚአብሔር እጅ በላዬ መጣች።


አካሉ እንደ ቢረሌ፣ ፊቱ እንደ መብረቅ፣ ዐይኖቹ እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹ እንደ ጋለ ናስ የሚያብረቀርቁ፣ ድምፁም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበር።


跟着我们:

广告


广告