Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 7:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ፍጻሜ መጥቷል! ፍጻሜ መጥቷል! በአንቺ ላይ ተነሣሥቷል፤ እነሆ፤ ደርሷል!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ፍጻሜ መጥቷል፥ ፍጻሜ መጥቷል፥ በአንቺ ላይ ነቅቷል፥ እነሆ፥ መጥቷል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 መጨረሻው መጥቶአል፤ መጨረሻው ደርሶአል፤ በእናንተ ላይ ተነሥቶአል፤ እነሆ፥ መጥቶአል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ፍጻሜ መጥ​ቶ​አል፤ ፍጻሜ መጥ​ቶ​አል፤ ነቅ​ቶ​ብ​ሻል፤ እነሆ ደር​ሶ​አል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ፍጻሜ መጥቶአል፥ ፍጻሜ መጥቶአል፥ ነቅቶብሻል፥ እነሆ፥ ደርሶአል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 7:6
11 交叉引用  

ለመልካም ሳይሆን ለክፉ እተጋባቸዋለሁና፤ በግብጽ የሚኖሩ አይሁድ ፈጽሞ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ይደመሰሳሉ።


ሰዎች እግር እግራችንን ተከታተሉን፤ ስለዚህ በመንገዳችን መሄድ አልቻልንም፤ መጨረሻችን ቀርቧል፤ ቀኖቻችንም ተቈጥረዋል፤ ፍጻሜያችን መጥቷልና።


እንዲህ በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ይህን አባባል እሽራለሁ፤ በእስራኤልም ምድር ዳግመኛ በንግግራቸው አይጠቀሙበትም።” እንዲህም በላቸው፤ “ራእዩ ሁሉ የሚፈጸምበት ጊዜ ቀርቧል፤


“ ‘አንተ የግፍ ጽዋህ የሞላ፣ የምትቀጣበት ቀን የደረሰ፣ ርኩስና ክፉ የእስራኤል መስፍን ሆይ፤


እነሆ ይመጣል! በርግጥም ይሆናል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ያ ያልሁት ቀን ይህ ነው።


“ ‘እነሆ ቀኑ ይኸው ደረሰ! የጥፋት ፍርድ ተገልጧል፤ በትሩ አቈጥቍጧል፤ ትዕቢት አብቧል።


አሁንም መጨረሻሽ ደርሷል፤ ቍጣዬን በአንቺ ላይ አፈስሳለሁ፤ እንደ አካሄድሽ እፈርድብሻለሁ፤ ስለ ጸያፍ ተግባርሽ ሁሉ፣ ተገቢውን ቅጣት እከፍልሻለሁ።


እናንተ በምድሪቱ የምትኖሩ ሆይ፤ የጥፋት ፍርድ መጥቶባችኋል፤ ጊዜው ደርሷል፤ በተራሮች ላይ እልልታ ሳይሆን ሽብር የሚሰማበት ቀን ቀርቧል።


እርሱም፣ “አሞጽ ሆይ፤ ምን ታያለህ?” አለኝ። እኔም፣ “የጐመራ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት አያለሁ” አልሁ። ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፍጻሜ መጥቷል፤ ከእንግዲህም አልምራቸውም።”


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰይፍ ሆይ፤ በእረኛዬ፣ በቅርብ ወዳጄ ላይ ንቃ! እረኛውን ምታ፣ በጎቹም ይበተናሉ፤ እኔም ክንዴን ወደ ታናናሾቹ አዞራለሁ።”


የጽድቅ ሰባኪ የነበረውንም ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋራ አድኖ፣ ለቀድሞው ዓለም ሳይራራ በኀጢአተኞች ላይ የጥፋት ውሃ ካመጣ፣


跟着我们:

广告


广告