Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 7:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ማቅ ይለብሳሉ፤ ሽብርም ይውጣቸዋል። ፊታቸው ኀፍረት ይለብሳል፤ ራሳቸውም ይላጫል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ማቅ ይለብሳሉ፥ ድንጋጤም ይሸፍናቸዋል፥ በሁሉም ፊቶች ላይ እፍረት ይሆናል፥ ራሳቸውም ሁሉ መላጣ ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ማቅ ይለብሳሉ፤ ድንጋጤ ይይዛቸዋል፤ በፊቶቻቸው ላይ ኀፍረት ይታያል፤ ራሳቸውንም ይላጫሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ማቅም ትታ​ጠ​ቃ​ላ​ችሁ፤ ድን​ጋ​ጤም ይሸ​ፍ​ና​ች​ኋል፤ በፊ​ትም ሁሉ ላይ ሐፍ​ረት ይሆ​ናል፤ በራ​ሳ​ች​ሁም ሁሉ ላይ ቡሃ​ነት ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ማቅም ይለብሳሉ ድንጋጤም ይሸፍናቸዋል፥ በፊትም ሁሉ ላይ እፍረት ይሆናል፥ ራሳቸውንም ሁሉ ይነጩታል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 7:18
14 交叉引用  

ፀሓይ ልትገባ ስትል አብራም እንቅልፍ ወሰደው፤ የሚያስፈራም ድቅድቅ ጨለማ መጣበት።


ስለዚህ ነገር ባሰብሁ ቍጥር እደነግጣለሁ፤ ሰውነቴም በፍርሀት ይንቀጠቀጣል።


በጭንቀቴ ደስ የሚላቸው፣ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤ በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣ ዕፍረትንና ውርደትን ይከናነቡ።


በሽቱ ፈንታ ግማት፣ በሻሽ ፈንታ ገመድ፣ አምሮ በተሠራ ጠጕር ፈንታ ቡሓነት፣ ባማረ ልብስ ፈንታ ማቅ፣ በውበትም ፈንታ ጠባሳ ይሆናል።


እንግዲህ ዕፍረታችንን ተከናንበን እንተኛ፤ ውርደታችንም ይሸፍነን፤ እኛም አባቶቻችንም፣ እግዚአብሔር አምላካችንን በድለናልና፤ ከልጅነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አምላካችንን እግዚአብሔርን አልታዘዝንም።”


የእያንዳንዱ ሰው ራስ፣ ጢምም ሁሉ ተላጭቷል፤ እጅ ሁሉ ተቸፍችፏል፤ ወገብም ሁሉ ማቅ ታጥቋል።


ጠላት ሰይፍ ታጥቋል፤ በየቦታውም ሽብር ሞልቷል፤ ስለዚህ ወደ ውጭ አትውጡ፤ በየመንገዱ አትዘዋወሩ።


የሕዝቤ ልጅ ሆይ፤ ማቅ ልበሺ፤ በዐመድም ላይ ተንከባለዪ፤ አንድያ ልጁን እንዳጣ ሰው፣ ምርር ብለሽ አልቅሺ፤ አጥፊው በድንገት፣ በላያችን ይመጣልና።


ስለ አንቺ ጠጕራቸውን ይላጫሉ፤ ማቅም ይለብሳሉ፤ በነፍስ ምሬት፣ በመራራም ሐዘን ያለቅሱልሻል።


ካህናት ሆይ፤ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ፤ እናንተ በመሠዊያው ፊት የምታገለግሉ፣ ዋይ በሉ፤ እናንተ በአምላኬ ፊት የምታገለግሉ፣ ኑ፤ ማቅ ለብሳችሁ ዕደሩ፤ የእህል ቍርባኑና የመጠጥ ቍርባኑ፣ ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጧልና።


ዓመት በዓላችሁን ወደ ልቅሶ፣ ዝማሬአችሁንም ሁሉ ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ሁላችሁም ማቅ እንድትለብሱ፣ ጠጕራችሁንም እንድትላጩ አደርጋለሁ፤ ያን ጊዜ ለአንድያ ልጅ ሞት እንደሚለቀስበት፣ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።”


跟着我们:

广告


广告