ሕዝቅኤል 6:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 የታረዱት ሰዎቻቸው በመሠዊያው ዙሪያ በጣዖቶቻቸው መካከል፣ ከፍ ባሉ ኰረብቶች ሁሉና በተራሮች ዐናት ሁሉ ላይ፣ በለመለመ ዛፍ ሁሉና ቅጠሉ በበዛ ወርካ ሁሉ ሥር፣ በአጠቃላይ ለጣዖቶቻቸው ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን ባቀረቡበት ስፍራ ሁሉ ተጥለው ሲታዩ፣ ያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ሬሳዎቻቸው በጣዖቶቻቸው መካከልና በመሠዊያዎቻቸው ዙሪያ፥ በረዣዥም ኮረብታ ሁሉ፥ በተራሮችም ራሶች ሁሉ፥ ከለመለመውም ዛፍ ሁሉ ሥርና ቅጠሉም ከበዛ ባሉጥ ሁሉ ሥር ለጣዖቶቻቸው ጣፋጭ ሽታ ባቀረቡበት ስፍራ በወደቁ ጊዜ ያኔ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ሬሳዎች በጣዖቶችና በመሠዊያዎች ዙሪያ ይከመራሉ፤ በከፍተኛ ኰረብቶችና በተራሮች ጫፍ ላይ፥ እንዲሁም በየለምለሙ ዛፍና በየትልልቁ ወርካ ሥር ለጣዖቶቻቸው መልካም ሽታ ባቀረቡባቸው ስፍራዎች ሁሉ ሬሳዎች ይወድቃሉ፤ በዚያን ጊዜ ሰዎች ሁሉ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ሬሳዎቻቸው በጣዖቶቻቸው መካከልና በመሠዊያዎቻቸው ዙሪያ በወደቁ ጊዜ በረዣዥም ኮረብታ ሁሉ፥ በተራሮችም ራሶች ሁሉ፥ በዕንጨቱም ጥላ ሥር ለጣዖቶቻቸው ሁሉ፥ መልካም መዓዛን ባጠኑበት ከቅጠሉ ሁሉ በታች ሬሳዎቻቸው በወደቁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ተወግተውም የሞቱ ሰዎቻቸው በጣዖቶቻቸው መካከልና በመሠዊያዎቻቸው ዙሪያ፥ ለጣዖቶቻቸው ጣፋጭ ሽታ ባቀረቡበት ስፍራ፥ ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ በተራሮችም ራስ ሁሉ ላይ፥ ከለመለመውም ዛፍ ሁሉ በታች ቅጠሉም ከበዛ ከአድባር ዛፍ ሁሉ በታች በሆኑ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። 参见章节 |