Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 48:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 “በተቀደሰው ድርሻና በከተማዪቱ ቦታ ግራና ቀኝ ያለው ቀሪ ቦታ፣ ለገዢው ይሆናል፤ ይህም ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ከሆነው ከተቀደሰው ቦታ አንሥቶ በምሥራቅ በኩል እስከ ምሥራቁ ወሰን ይዘልቃል፤ በምዕራቡም በኩል እንዲሁ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ከሆነው ይዞታ አንሥቶ እስከ ምዕራቡ ወሰን ይዘልቃል። የየነገዱ ድርሻ ከሆነውም መሬት ጐን ለጐን የሚሄዱት ቦታዎች የገዢው ይሆናሉ። የተቀደሰው ቦታና መቅደሱ በመካከላቸው ይሆናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ በዚህና በዚያ ወገን የቀረው ለአለቃው ይሆናል፤ በመባው በሃያ አምስቱ ሺህ ፊት ወደ ምሥራቁ ድንበር፥ በምዕራብም በኩል በሀያ አምስቱ ሺህ ፊት ወደ ምዕራቡ ድንበር፥ እንደ ዕጣ ክፍሎች ሁሉ መጠን፥ ለአለቃው ይሆናል፤ የተቀደሰውም መባና ቤተ መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በተቀደሰው ቦታና በከተማውም ይዞታ በሁለቱም በኩል የተረፈው ክፍል የመስፍኑ ድርሻ ነው። ይኸውም በምሥራቅ በኩል የተቀደሰውን ቦታ ከሚያዋስነው ኻያ አምስት ሺህ ክንድ ተነሥቶ እስከ ምድሪቱ ወሰን ድረስ ነው። በምዕራብም በኩል የተቀደሰውን ቦታ ከሚያዋስነው ከኻያ አምስት ሺህ ክንድ ተነሥቶ እስከ ምድሪቱ ወሰን ድረስ ነው። የመሪውም ድርሻ ርዝመቱ ከሌሎቹ ነገዶች ድርሻ እኩል ነው። በዚህ ዐይነት የተቀደሰው ቦታና ቤተ መቅደሱ በመካከል ይሆናሉ ማለት ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 “በተ​ቀ​ደ​ሰው መባና በከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ፥ በዚ​ህና በዚያ ወገን የቀ​ረው ለአ​ለ​ቃው ይሆ​ናል፤ በመ​ባው በሃያ አም​ስት ሺህ ፊት እስከ ምሥ​ራቁ ድን​በር፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል በሃያ አም​ስት ሺህ ፊት እስከ ምዕ​ራቡ ድን​በር፥ እንደ ዕጣ ክፍል ሁሉ መጠን፥ ለአ​ለ​ቃው ይሆ​ናል፤ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም መባና ቤተ መቅ​ደሱ በመ​ካ​ከሉ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በተቀደሰው መባና በከተማይቱ ይዞታ በዚህና በዚያ ወገን የቀረው ለአለቃው ይሆናል፥ በመባው በሃያ አምስቱ ሺህ ፊት ወደ ምሥራቁ ድንበር፥ በምዕራብም በኩል በሀያ አምስቱ ሺህ ፊት ወደ ምዕራቡ ድንበር፥ እንደ ዕጣ ክፍል ሁሉ መጠን፥ ለአለቃው ይሆናል፥ የተቀደሰውም መባና ቤተ መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 48:21
8 交叉引用  

“ ‘ባሪያዬ ዳዊት በላያቸው ይነግሣል፤ ሁሉም አንድ እረኛ ይኖራቸዋል፤ ሕጌን ይከተላሉ፤ ሥርዐቴንም በጥንቃቄ ይጠብቃሉ።


ይህ ለካህናቱ የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ፣ በምዕራብ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺሕ ክንድ በምሥራቅ በኩል ወርዱ ዐሥር ሺሕ ክንድ ሲሆን፣ በደቡብ በኩል ርዝመቱ ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ይሆናል፤ የእግዚአብሔርም መቅደስ በመካከሉ ይቆማል።


አጠቃላይ ይዞታው በአራቱም ማእዘን እኩል ሲሆን፣ እያንዳንዱ ማእዘን ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ነው፤ ከከተማዪቱ ድርሻ ጋራ የተቀደሰውን ክፍል ልዩ መባ በማድረግ ታስቀምጣላችሁ።


ስለዚህ የሌዋውያኑ ይዞታና የከተማዪቱ ይዞታ ለገዢው በተሰጠው ቦታ መካከል ይሆናል፤ የገዢው ቦታም በይሁዳ ድንበርና በብንያም ድንበር መካከል ይሆናል።


“ይሁዳን ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ የሚያዋስነው ምድር ለመባ የሚቀርብ ድርሻ ይሆናል፤ ስፋቱም ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ነው፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያለውም ርዝመቱ፣ ከነገዶቹ ድርሻ እንደ አንዱ ሆኖ፣ መቅደሱ በመካከሉ ይሆናል።


የይሁዳ ሕዝብና የእስራኤል ሕዝብ እንደ ገና አንድ ይሆናሉ፤ አንድ መሪም ይሾማሉ፤ አንድ ሆነውም በምድሪቱ ይገንናሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።


跟着我们:

广告


广告