ሕዝቅኤል 47:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ቀጥሎም አንድ ሺሕ ክንድ ለካ፤ እስከ ጕልበት ወደሚደርስም ውሃ መራኝ፤ ከዚያም ሌላ አንድ ሺሕ ክንድ ለካ፤ እስከ ወገብ ወደሚደርስም ውሃ መራኝ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 እንደገና አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሳለፈኝ፥ ውኃውም እስከ ጉልበት ድረስ ነበር። ደግሞም አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሳለፈኝ፥ ውኃውም እስከ ወገብ ድረስ ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እንደገናም አንድ ሺህ ክንድ ለካና እንድራመድ አደረገኝ፤ ውሃውም እስከ ጒልበቴ ደረሰ፤ ቀጥሎም አንድ ሺህ ክንድ ለክቶ በውሃው ውስጥ እንድራመድ አደረገኝ፤ ውሃውም እስከ ወገቤ ደረሰ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ደግሞ አንድ ሺህ ለካ፤ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፤ ውኃውም እስከ ጉልበት ደረሰ፤ ደግሞም አንድ ሺህ ለካ፤ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፤ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ደግሞ አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ጕልበት ደረሰ። ደግሞም አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ። 参见章节 |