Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 46:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ገዥው በሰንበት ቀን በእግዚአብሔር ፊት የሚያቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ስድስት የበግ ጠቦትና አንድ አውራ በግ ነው፤ ሁሉም እንከን የሌላቸው ይሁኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 መስፍኑ በሰንበት ቀን ለጌታ የሚያቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸው ስድስት የበግ ጠቦቶችና ነውር የሌለበት አንድ አውራ በግ ይሁን፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 “መስፍኑ በሰንበት ቀን በሙሉ ለሚቃጠል መሥዋዕት ምንም ነውር የሌለባቸውን ስድስት የበግ ጠቦቶችና አንድ የበግ አውራ ለእግዚአብሔር ያቅርብ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 አለ​ቃ​ውም በሰ​ን​በት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​በው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው ስድ​ስት የበግ ጠቦ​ቶች፥ ነው​ርም የሌ​ለ​በት አንድ አውራ በግ ይሁን፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 አለቃውም በሰንበት ቀን ለእግዚአብሔር የሚያቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለባቸው ስድስት የበግ ጠቦቶች ነውርም የሌለበት አንድ አውራ በግ ይሁን፥

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 46:4
4 交叉引用  

በበዓላት፣ በወር መባቻና በሰንበታት፣ ለእስራኤል ቤት በተወሰኑት በዓላት ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባንና የመጠጥ ቍርባን ማቅረብ የገዢው ኀላፊነት ነው፤ ለእስራኤል ቤት ማስተስረያ እንዲሆንም የኀጢአት መሥዋዕት፣ የእህል ቍርባን፣ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ያቀርባል።’


በዚያም ቀን ገዥው ስለ ራሱና ስለ ምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ አንድ ወይፈን የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል።


ከእያንዳንዱ ወይፈን ጋራ ለመጠጥ ቍርባን የሚሆን የሂን ግማሽ የወይን ጠጅ፣ ከአውራው በግ ጋራ የሂን አንድ ሦስተኛ፣ ከእያንዳንዱም የበግ ጠቦት ጋራ የኢን አንድ አራተኛ የወይን ጠጅ ይቅረብ፤ ይህም በየወሩ መባቻ ዓመቱን ሙሉ የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።


跟着我们:

广告


广告