ሕዝቅኤል 42:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም12 በደቡብ በኩል ያሉት ክፍሎች በሮች መጠናቸው ተመሳሳይ ነበር። ከመመላለሻው መነሻ ላይ መግቢያ በር አለ፤ መመለሻውም ፊት ለፊት ካለው ወደ ምሥራቅ ከሚያመራው ግንብ ጋራ ተጓዳኝ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 በደቡብም በኩል ካሉት ክፍሎች በታች በምሥራቅ በኩል በቅጥሩ ራስ አጠገብ መግቢያ ነበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ስለዚህ በደቡብ በኩል ወዳሉት ክፍሎች መግቢያ በሮች የሚገባው በትይዩ በስተምሥራቅ ባለው ተመሳሳይ ግንብ መጨረሻ በሚገኘው መተላለፊያ በኩል ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 በደቡብም በኩል ከአሉት ዕቃ ቤቶች በታች በምሥራቅ በኩል በቅጥሩ ራስ አጠገብ መግቢያ በር ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 በደቡብም በኩል ካሉት ዕቃ ቤቶች በታች በምሥራቅ በኩል በቅጥሩ ራስ አጠገብ መግቢያ ነበረ። 参见章节 |