Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 41:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እርሱም የውስጠኛውን መቅደስ ርዝመት ለካ፤ ሃያ ክንድ ነበር፤ ወርዱም የውጪውን ግድግዳ ጨምሮ ሃያ ክንድ ነበር፤ እርሱም፣ “ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው” አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በመቅደሱ ፊት ያለውን ርዝመቱን ሀያ ክንድ ወርዱንም ሀያ ክንድ አድርጎ ለካና፦ “ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው” አለኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከመካከለኛው ክፍል ባሻገር ያለውን ውስጠኛ ክፍል ከማእዘን እስከ ማእዘን ሲለካ ርዝመቱ ኻያ ክንድ ወርዱም ኻያ ክንድ ሆነ፤ ከዚያም በኋላ “ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው” አለኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በመ​ቅ​ደ​ሱም ፊት ርዝ​መ​ቱን አርባ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም ሃያ ክንድ አድ​ርጎ ለካና፥ “ይህ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ነው” አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በመቅደሱም ፊት ርዘመቱን ሀያ ክንድ ወርዱንም ሀያ ክንድ አድርጎ ለካና፦ ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው አለኝ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 41:4
11 交叉引用  

በቤተ መቅደሱም ውስጥ በስተኋላ በኩል፣ ሃያውን ክንድ ቅድስተ ቅዱሳን እንዲሆን፣ ከወለሉ አንሥቶ እስከ ጣራው ድረስ በዝግባ ሳንቃዎች ጋረደው፤


ቅድስተ ቅዱሳኑም ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ ሃያ ክንድ፣ ቁመቱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ውስጡን በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ ከዝግባ የተሠራውንም መሠዊያ በወርቅ ለበጠው።


በዋናው ቤተ መቅደስና በቅድስተ ቅዱሳኑ ግድግዳ ዙሪያ ልዩ ክፍሎች ያሉት ተቀጥላ ግንብ ሠራ።


ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ጽዋዎችን፣ የመብራት መኰስተሪያዎችን፣ ለመርጫ የሚሆኑ ጐድጓዳ ሳሕኖችን፣ ጭልፋዎችን፣ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎችን፣ ለውስጠኛው ክፍል ለቅድስተ ቅዱሳኑ በሮችና እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ በሮች የሚሆኑ የወርቅ ማጠፊያዎችን።


ከዚያም ካህናቱ የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት አምጥተው የቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ አግብተው ከኪሩቤል ክንፍ በታች ባለው ስፍራው አኖሩት።


እንደዚሁም ቅድስተ ቅዱሳኑን ሠራ፤ ርዝመቱ ከቤተ መቅደሱ ወርድ ጋራ እኩል ሲሆን፣ ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ስፋቱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ውስጡንም በስድስት መቶ መክሊት የተጣራ ወርቅ ለበጠው።


ከዚያም ካህናቱ የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት አምጥተው የቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ አግብተው ከኪሩቤል ክንፍ በታች ባለው ስፍራው አኖሩት።


የውስጡ መቅደስና ቅድስተ ቅዱሳኑ እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት በር አላቸው፤


ከተማዪቱም ርዝመቷና ስፋቷ እኩል ሆኖ አራት ማእዘን ነበረች። እርሱም ከተማዪቱን በዘንጉ ለካ፤ ርዝመቷም ዐሥራ ሁለት ሺሕ ምዕራፍ ሆነ፤ ስፋቷና ከፍታዋም እንዲሁ ሆነ።


跟着我们:

广告


广告