ሕዝቅኤል 41:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ሦስት ክንድ ቁመት፣ ሁለት ክንድ ወርድ፣ ሁለት ክንድ ርዝመት ያለው የዕንጨት መሠዊያ ነበር፤ ማእዘኖቹ፣ መሠረቱና ጐኖቹ ሁሉ ከዕንጨት የተሠሩ ነበሩ። ሰውየውም፣ “ይህች በእግዚአብሔር ፊት ያለች ገበታ ናት” አለኝ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ከእንጨት የተሠራው መሠዊያ ቁመቱ ሦስት ክንድ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ነበር፥ ማዕዘኖቹ፥ እግሩና ግድግዳው ከእንጨት የተሠሩ ነበሩ፤ እርሱም፦ “ይህ በጌታ ፊት ያለ ገበታ ነው” አለኝ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 በቅድስተ ቅዱሳኑ መግቢያ ፊት ለፊት፥ ከእንጨት የተሠራ መሠዊያ የሚመስል ነገር ይታይ ነበር፤ እርሱም እኩልነት ያለው አራት ማእዘን ሲሆን፥ እያንዳንዱ ማእዘን ሁለት ክንድ ነበር፤ ከፍታውም ሦስት ክንድ ነበር፤ የማእዘን መደገፊያ ምሰሶዎቹ፥ መሠረቱና ጐኖቹ ሁሉ ከእንጨት የተሠሩ ነበሩ፤ ያም ሰው “ይህ በእግዚአብሔር ፊት የሚገኝ ጠረጴዛ ነው” አለኝ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 መሠዊያውም ቁመቱ ሦስት ክንድ፥ ርዝመቱ ሁለት ክንድ፥ ወርዱም ሁለት ክንድ ሆኖ ከእንጨት ተሠርቶ ነበር፤ ማዕዘኖቹም፥ እግሩም፥ አገዳዎቹም ከእንጨት ተሠርተው ነበር፤ እርሱም፥ “በእግዚአብሔር ፊት ያለችው ገበታ ይህች ናት” አለኝ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 መሠዊያውም ቁመቱ ሦስት ክንድ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ወርዱም ሁለት ክንድ ሆኖ ከእንጨት ተሠርቶ ነበር፥ ማዕዘኖቹም እግሩም አገዳዎቹም ከእንጨት ተሠርተው ነበር፥ እርሱም፦ በእግዚአብሔር ፊት ያለችው ገበታ ይህች ናት አለኝ። 参见章节 |