ሕዝቅኤል 40:40 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም40 ከመግቢያው በር ላይ ባለው መተላለፊያ በረንዳ በስተ ውጭው ግንብ ወደ ሰሜን በር መግቢያ ላይ ባሉት ደረጃዎች አጠገብ ከግራና ከቀኝ ሁለት ሁለት ጠረጴዛዎች ይገኛሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 ከመተላለፊያው በስተ ውጭ በሰሜን በኩል ባለው በር መግቢያ አጠገብ፥ ሁለት ገበታዎች ነበሩ፥ በበሩ መተላለፊያ በሌላኛው ወገን በኩል ሁለት ገበታዎች ነበሩ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 ከመግቢያው ክፍል በስተውጪ በሰሜን ቅጽር መግቢያ በር አጠገብ ሁለቱ በአንድ በኩል፥ ሁለቱ በሌላ በኩል በትይዩ የተቀመጡ አራት ተመሳሳይ ጠረጴዛዎች ነበሩ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 በሰሜን በኩል በአለው በር በስተውጭው፥ በመወጣጫው ደረጃዎች አጠገብ፥ በአንዱ ወገን ሁለት ገበታዎች ነበሩ፤ በሌላውም ወገን በበሩ ደጀ ሰላም በኩል ሁለት ገበታዎች ነበሩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 በሰሜን በኩል ባለው በር በስተ ውጭው፥ በመወጣጫው ደረጃዎች አጠገብ፥ በአንድ ወገን ሁለት ገበታዎች ነበሩ፥ በሌላውም ወገን በበሩ ደጀ ሰላም በኩል ሁለት ገበታዎች ነበሩ። 参见章节 |