Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 4:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እርሱም፣ “መልካም ነው፤ በሰው ዐይነ ምድር ሳይሆን፤ እንጀራህን በከብት ኵበት እንድትጋግር ፈቅጄልሃለሁ” አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ተመልከት በሰው ፋንድያ ፈንታ ኩበት ሰጥቼሃለሁ፥ ምግብህንም በእርሱ አዘጋጅ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እግዚአብሔርም “መልካም ነው፤ እንግዲያውስ በሰው ዐይነ ምድር ፈንታ የእንስሶችን ኩበት ወስደህ እርሱን በማቀጣጠል እንጀራ ጋግር” አለኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እር​ሱም፥ “እነሆ በሰው ኵስ ፋንታ የከ​ብት ኩበት ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም እን​ጀ​ራ​ህን ትጋ​ግ​ራ​ለህ” አለኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እርሱም፦ እነሆ፥ በሰው ፋንድያ ፋንታ ኩበት ሰጥቼሃለሁ በእርሱም እንጀራህን ትጋግራለህ አለኝ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 4:15
4 交叉引用  

ነገር ግን የጦር አዛዡ መልሶ፣ “ጌታዬ እነዚህን ቃሎች እንድናገር የላከኝ ለጌታህና ለአንተ ብቻ ነበርን? እንደ እናንተ የራሳቸውን ኵስ ለመብላትና ሽንታቸውንም ለመጠጣት በቅጥሩ ላይ ለተቀመጡት ሰዎችም አይደለምን?” አላቸው።


እንጀራ በመፈለግ፣ ሕዝቧ ሁሉ በሥቃይ ይጮኻል፤ በሕይወት ለመኖር፣ የከበረ ሀብታቸውን በምግብ ይለውጣሉ፤ “አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ አስበኝ፤ ተመልከተኝም፤ እኔ ተዋርጃለሁና።”


እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ወይኔ! ከቶ ረክሼ አላውቅም፤ ከልጅነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ጥንብ ወይም አውሬ የጣለውን በልቼ አላውቅም፤ ርኩስ ሥጋም በአፌ አልገባም” አልሁ።


ደግሞም እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ የኢየሩሳሌምን የምግብ ምንጭ አደርቃለሁ፤ ሕዝቡም የተወሰነ ምግብ በጭንቀት ይበላል፤ የተመጠነ ውሃም በሥጋት ይጠጣል።


跟着我们:

广告


广告