Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 39:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ ‘ከዚያም በእስራኤል ከተሞች የሚኖሩ ሁሉ ወጥተው የጦር መሣሪያውን፣ ትልልቁንና ትንንሹን ጋሻ፣ ቀስቱን፣ ፍላጻውን፣ የጦር ዱላውንና ጦሩን ሰብስበው ማገዶ በማድረግ ያነድዱታል፤ ሰባት ዓመት ይማግዱታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በእስራኤልም ከተሞች የሚኖሩ ወጥተው፥ የጦር መሣሪያዎችን፥ አላባሽ ጋሻንና ጋሻን፥ ቀስትና ፍላጻዎችን፥ የእጅ በትሮችንና ጦርንም በእሳት ያቃጥላሉ፤ ሰባት ዓመት በእሳት ያቃጥሉአቸዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በእስራኤል ከተሞች የሚኖሩ ሕዝብ ወጥተው የተጣለውን የጦር መሣሪያ ሁሉ ለእሳት ማገዶ እንዲሆን ይሰበስባሉ፤ ጋሻውን፥ ቀስቱን፥ ፍላጻውን፥ ጦሩንና ዱላውን ሁሉ ሰብስበው ያነዱታል፤ ለሰባት ዓመት የሚበቃም ማገዶ ይኖራቸዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ከተ​ሞች የሚ​ኖሩ ይወ​ጣሉ፤ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ንም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላሉ፤ አላ​ባሽ አግሬ ጋሻ​ንና ጋሻን፥ ቀስ​ት​ንና ፍላ​ጻ​ዎ​ችን፥ የእጅ በት​ሮ​ች​ንና ጦር​ንም ያቃ​ጥ​ላሉ፤ ሰባት ዓመት በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በእስራኤልም ከተሞች የሚኖሩ ይወጣሉ፥ የጦር መሣሪያዎችንም በእሳት ያቃጥላሉ፥ አላባሽ ጋሻንና ጋሻን፥ ቀስትንና ፍላጻዎችን፥ ጎመድንና ጦርንም ያቃጥላሉ፥ ሰባት ዓመት በእሳት ያቃጥሉአቸዋል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 39:9
8 交叉引用  

ከዳር እስከ ዳር ጦርነትን ከምድር ያስወግዳል፤ ቀስትን ይሰብራል፤ ጦርን ያነክታል፤ ጋሻንም በእሳት ያቃጥላል።


“ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ የሚበሏቸው ትሎች አይሞቱም፤ የሚያቃጥላቸው እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።”


ከሜዳ ላይ ዕንጨት መልቀም፣ ከዱርም ዛፍ መቍረጥ አያስፈልጋቸውም፤ የጦር መሣሪያቸውን በመማገድ ይጠቀማሉና። የዘረፏቸውን ይዘርፋሉ፤ የበዘበዟቸውን ይበዘብዛሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


እነሆ ይመጣል! በርግጥም ይሆናል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ያ ያልሁት ቀን ይህ ነው።


ሠረገሎችን ከኤፍሬም፣ የጦር ፈረሶችን ከኢየሩሳሌም እወስዳለሁ፤ የጦርነቱም ቀስት ይሰበራል፤ ሰላምን ለአሕዛብ ያውጃል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፣ ከወንዙም እስከ ምድር ዳር ድረስ ይዘረጋል።


ይህንም በገዛ ዐይናችሁ ታያላችሁ፤ እናንተም፣ ‘ከእስራኤል ዳርቻ ወዲያ እንኳ እግዚአብሔር ታላቅ ነው!’ ትላላችሁ።


እግዚአብሔር ኢያሱን፣ “እነዚህን ሁሉ ነገ በዚች ሰዓት እንደ ሙት አድርጌ፣ በእስራኤል እጅ አሳልፌ ስለምሰጣቸው አትፍራቸው። የፈረሶቻቸውን ቋንጃ ትቈርጣለህ፤ ሠረገሎቻቸውንም ታቃጥላለህ” አለው።


跟着我们:

广告


广告