ሕዝቅኤል 39:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም14 “ ‘ሰዎች ምድሪቱን ለማጽዳት በየጊዜው ይቀጠራሉ። አንዳንዶቹ ምድሪቱን ያሥሣሉ፤ ከእነርሱም በተጨማሪ ሌሎች ሳይቀበሩ የቀሩትን ይቀብራሉ። ከሰባት ወር በኋላም ፍለጋ ይጀምራሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ምድሪቱን ለማጽዳት በምድሪቱ ላይ ዘወትር የሚመላለሱና በምድር ላይ ወድቀው የቀሩትን የሚቀብሩ ሰዎችን ይለያሉ፤ ከሰባቱ ወር በኋላ ፍለጋ ይጀምራሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ከሰባት ወራትም በኋላ በምድር ላይ የተረፉ ሬሳዎች ቢኖሩ በየስፍራው በመዘዋወር እየፈለጉ በመቅበር ምድሪቱን የሚያጸዱ ሰዎች ይመደባሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ምድርንም ለማጽዳት በምድሩ ላይ ወድቀው የቀሩትን የሚቀብሩ፥ ዘወትር በምድሩ ላይ የሚዞሩትን ሰዎች ይቀጥራሉ፤ ከሰባት ወርም በኋላ ይመረምራሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ምድርንም ለማጽዳት በምድሩ ላይ ወድቀው የቀሩትን የሚቀብሩ፥ ዘወትር በምድሩ ላይ የሚዞሩትን ሰዎች ይቀጥራሉ፥ ከሰባት ወርም በኋላ ይመረምራሉ። 参见章节 |