ሕዝቅኤል 39:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 “ ‘በዚያ ቀን ሰዎች በምሥራቅ በኩል ወደ ባሕሩ በሚጓዙበት ሸለቆ፣ ለጎግ የመቃብር ስፍራ በእስራኤል እሰጠዋለሁ። ጎግና ሰራዊቱ ሁሉ በዚያ ስለሚቀበሩ፣ የተጓዦችን መንገድ ይዘጋሉ፤ ስለዚህም የሐሞን ጎግ ሸለቆ ይባላል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 በዚያም ቀን በእስራኤል፥ በባሕሩ በምሥራቅ በኩል ባለው በመንገደኞች ሸለቆ ለጎግ የመቃብር ስፍራ እሰጠዋለሁ፤ በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ስለሚቀበሩ፥ የመንገደኞች መተላለፊያ ይዘጋል፤ “የሐሞን-ጎግ ሸለቆ” ተብሎ ይጠራል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ይህ ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ በእስራኤል ምድር በሚገኘው፥ ከሙት ባሕር በስተ ምሥራቅ ባለው በመንገደኞች ሸለቆ ውስጥ፥ ለጎግ የመቃብር ቦታ እሰጠዋለሁ፤ እርሱም ከብዛቱ የተነሣ መተላለፊያ መንገዱን ይዘጋል፤ ጎግና ሠራዊቱ ሁሉ በዚያ ይቀበራሉ፤ ስለዚህም ያ ሸለቆ ‘የጎግ ሠራዊት ሸለቆ’ ተብሎ ይጠራል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 “በዚያም ቀን በእስራኤል ዘንድ በባሕር ምሥራቅ የሚያልፉበትን ሸለቆ፥ የመቃብርን ስፍራ ለጎግ እሰጣለሁ፤ የሚያልፉትንም ይከለክላል፤ በዚያም ጎግንና ሠራዊቱን ሁሉ ይቀብራሉ፤ የሸለቆውንም ስም የጎግ መቃብር ብለው ይጠሩታል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 በዚያም ቀን በእስራኤል ዘንድ በባሕር ምሥራቅ የሚያልፉበትን ሸለቆ የመቃብርን ስፍራ ለጎግ እሰጣለሁ፥ የሚያልፉትንም ይከለክላል፥ በዚያም ጎግንና ብዛቱን ሁሉ ይቀብራሉ፥ የሸለቆውንም ስም ሐሞንጎግ ብለው ይጠሩታል። 参见章节 |