Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 38:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፤ ትንቢት ተናገር፤ ጎግንም እንዲህ በለው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በዚያ ቀን ሕዝቤ እስራኤል ያለ ሥጋት መቀመጡን ዐውቀህ አትንቀሳቀስምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ ጎግንም እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሕዝቤ እስራኤል በሰላም በተቀመጠ ጊዜ በዚያ ቀን አንተ አታውቀውምን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ የሰው ልጅ ሆይ! በጎግ ላይ እንዲህ ብለህ ትንቢት ተናገር፤ “ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘በዚያን ቀን ሕዝቤ እስራኤል በሰላም በሚኖሩበት ጊዜ አንተ ራስህን ታነሣሣለህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ጎግ​ንም እን​ዲህ በለው፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን ሕዝቤ እስ​ራ​ኤል በሰ​ላም በተ​ቀ​መጠ ጊዜ አንተ የም​ት​ነሣ አይ​ደ​ለ​ምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አንተ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ስለዚህ ትንቢት ተናገር ጎግንም እንዲህ በለው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ቀን ሕዝቤ እስራኤል ሳይፈራ በተቀመጠ ጊዜ አንተ አታውቀውምን?

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 38:14
10 交叉引用  

በርሱም ዘመን ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም ያለ ሥጋት ይኖራል፤ የሚጠራበትም ስም፣ “እግዚአብሔር ጽድቃችን” የሚል ይሆናል።


መቅደሴም ለዘላለም በመካከላቸው በሚሆንበት ጊዜ፣ አሕዛብ እኔ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ ቀደስሁ ያውቃሉ።’ ”


እንዲህም ትላለህ፤ “ቅጥር የሌላቸውን መንደሮች ምድር እወራለሁ፤ ሁሉም ያለ ቅጥር፣ ያለ በርና ያለ ብረት መወርወሪያ የሚኖረውን፣ ሰላማዊና ያለ ሥጋት የተቀመጠውን ሕዝብ እወጋለሁ፤


“የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን በማጎግ ምድር በሚገኘው፣ በሜሼኽና በቶቤል ዋና አለቃ በጎግ ላይ አድርግ፤ በርሱ ላይ ትንቢት ተናገር፤


ከብዙ ቀን በኋላ ለጦርነት ትጠራለህ። በኋለኛው ዘመንም ከጦርነት ያገገመችውን፣ ሕዝቧ ከአያሌ አሕዛብ መካከል ወጥቶ የተሰበሰበውን፣ ለብዙ ጊዜ ባድማ በነበረው በእስራኤል ተራሮች ላይ የሰፈረውን ወገን ትወርራለህ። ከሕዝቦች መካከል ወጥተው፣ አሁን ሁሉም ያለ ሥጋት ይኖራሉ።


“በዚያ ዘመን፣ በዚያ ጊዜ፣ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምርኮ ስመልስ፣


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለዚህ እስከምፈርድበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፤ አሕዛብን ላከማች፣ መንግሥታትን ልሰበስብ፣ መዓቴንና ጽኑ ቍጣዬን በላያቸው ላፈስስ ወስኛለሁ። በቅናቴ ቍጣ እሳት፣ መላዋ ምድር ትቃጠላለችና።


እኔ ራሴ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ’ ይላል እግዚአብሔር፣ ‘በውስጧም ክብሯ እሆናለሁ።’


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “ካከበረኝና በዘረፏችሁ አሕዛብ ላይ ከላከኝ በኋላ፣ የሚነካችሁ የዐይኑን ብሌን ይነካል፤


跟着我们:

广告


广告