Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 37:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እንዲህ በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በኤፍሬም እጅ ያለውን የዮሴፍን በትርና የተባባሪዎቹን የእስራኤላውያንን ነገድ በትር እወስዳለሁ፤ ከይሁዳ በትር ጋራ አጋጥሜ አንድ ወጥ በትር አደርጋቸዋለሁ፤ እነርሱም በእጄ አንድ በትር ይሆናሉ።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በኤፍሬም እጅና በተባባሪዎቹ በእስራኤል ነገዶች ያለውን የዮሴፍን በትር እወስዳለሁ፥ ከይሁዳ በትር ጋር አስቀምጣቸዋለሁ፥ አንድ በትር አደርጋቸዋለሁ፥ በእጄም አንድ ይሆናሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል ብለህ ንገራቸው፦ በኤፍሬም እጅ ያለውን የዮሴፍን ከእነርሱ ጋር የተባበሩትን የእስራኤልን በትር ወስጄ አንድ በትር እንዲሆኑ ከይሁዳ በትር ጋር አጋጥማቸውና በእጄ አንድ ይሆናሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እነሆ በኤ​ፍ​ሬም እጅ ያለ​ውን የዮ​ሴ​ፍን በትር ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገ​ዶች እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ከይ​ሁዳ በትር ጋር አጋ​ጥ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አንድ በት​ርም አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ጄም ውስጥ አንድ ይሆ​ናሉ በላ​ቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በኤፍሬም እጅ ያለውን የዮሴፍን በትር ባልንጀሮቹንም የእስራኤልን ነገዶች እወስዳለሁ፥ ከእርሱም ከይሁዳ በትር ጋር አጋጥማቸዋለሁ አንድ በትርም አደርጋቸዋለሁ፥ በእጄም ውስጥ አንድ ይሆናሉ በላቸው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 37:19
8 交叉引用  

በዚያ ዘመን የይሁዳ ቤትና የእስራኤል ቤት በአንድነት ሆነው ከሰሜን ምድር ለአባቶቻቸው ርስት አድርጌ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይመጣሉ።


“የአገርህ ልጆች፣ ‘ይህስ ምን ማለትህ እንደ ሆነ አትነግረንምን?’ ብለው ሲጠይቁህ፣


የጻፍህባቸውን በትሮች ከፊት ለፊታቸው ያዝ፤


“የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፤ የዮሴፍንም ቤት እታደጋለሁ። ስለምራራላቸው፣ ወደ ቦታቸው እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም በእኔ እንዳልተተዉ ሰዎች ይሆናሉ፤ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝና፣ ጸሎታቸውን እሰማለሁ።


በዚያ ግሪክ ወይም ይሁዲ፣ የተገረዘ ወይም ያልተገረዘ፣ አረማዊ ወይም እስኩቴስ፣ ባሪያ ወይም ጌታ ብሎ ልዩነት የለም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉም ነው፤ በሁሉም ነው።


跟着我们:

广告


广告