ሕዝቅኤል 37:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 “የሰው ልጅ ሆይ፤ አንድ በትር ወስደህ፣ ‘የይሁዳና የተባባሪዎቹ የእስራኤላውያን’ ብለህ ጻፍበት። ከዚያም ሌላ በትር ወስደህ፣ ‘የኤፍሬም፣ የዮሴፍና የተባባሪዎቹ የእስራኤል ቤት ሁሉ’ ብለህ ጻፍበት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 አንተ የሰው ልጅ ሆይ፥ አንድ በትር ለራስህ ውሰድ፥ በላዩ “ለይሁዳና ለተባባሪዎቹ የእስራኤል ልጆች” ብለህ ጻፍበት፤ ሌላም በትር ውሰድ፦ በላዩም “የኤፍሬም በትር ለሆነው ለዮሴፍና ለተባባሪዎቹ፥ ለመላው የእስራኤል ቤት” ብለህ ጻፍበት። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 “የሰው ልጅ ሆይ! አንድ በትር ወስደህ ‘በእርሱ ላይ ለይሁዳና ከእርሱ ጋር ለተባበሩ እስራኤላውያን’ ብለህ ጻፍ፤ ከዚያም ሌላ በትር ወስደህ በእርሱ ላይ ‘ለዮሴፍ ማለት ለኤፍሬምና ከእርሱ ጋር ለተባበሩ እስራኤላውያን’ ብለህ ጻፍ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 “አንተ የሰው ልጅ ሆይ! አንድ በትር ውሰድና፦ ይሁዳንና ባልንጀሮቹን፥ የእስራኤልንም ልጆች በላዩ ጻፍ፤ ሌላም በትር ውሰድና፦ የኤፍሬም በትር ለዮሴፍና ለባልንጀሮቹ ለእስራኤል ቤት ሁሉ ብለህ በላዩ ጻፍ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 አንተ፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ አንድ በትር ውሰድና፦ ለይሁዳና ለባንጀሮቹ ለእስራኤል ልጆች ብለህ በላዩ ጻፍ፥ ሌላም በትር ውሰድና፦ የኤፍሬም በትር ለዮሴፍና ለባልንጀሮቹ ለእስራኤል ቤት ሁሉ ብለህ በላዩ ጻፍ። 参见章节 |