Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 36:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ ‘የእስራኤል ተራሮች ሆይ፣ እናንተ ግን፤ ለሕዝቤ ለእስራኤል ቅርንጫፍ ታወጣላችሁ፤ ፍሬም ታፈራላችሁ፤ በቅርቡ ወደ አገራቸው ይመለሳሉና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እናንተም የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ ቅርንጫፎችን ታቆጠቁጣላችሁ፥ ለሕዝቤ ለእስራኤል ፍሬአቸሁን ትሰጣላችሁ ለመምጣት ቀርበዋልና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለ እናንተ ስለ ሕዝቤ እስራኤል ግን የምለው ይህ ነው፤ በእስራኤል ተራራዎች ላይ የሚገኙ ዛፎች ሁሉ እንደገና ይለመልማሉ፤ ፍሬም ይሰጡአችኋል፤ እናንተም በፍጥነት ወደ አገራችሁ ትመለሳላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “የእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ሆይ! ሕዝቤ ይመጡ ዘንድ ተስፋ ያደ​ር​ጋ​ሉና ወይ​ና​ች​ሁ​ንና ፍሬ​ያ​ች​ሁን ይበ​ላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የእስራኤል ተራሮች ሆይ፥ እናንተ ግን ቅርንጫፎቻችሁን ታቈጠቍጣላችሁ፥ ይመጡም ዘንድ ቀርበዋልና ለሕዝቤ ለእስራኤል ፍሬአቸሁን ትሰጣላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 36:8
17 交叉引用  

ምድር ፍሬዋን ሰጠች፤ እግዚአብሔር፣ አምላካችን ይባርከናል።


እግዚአብሔር በጎ ነገር ይለግሳል፤ ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች።


በሚመጡት ቀናት ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፤ እስራኤልም ያቈጠቍጣል፣ ያብባልም፤ በፍሬአቸውም ምድርን ሁሉ ይሞላሉ።


በምድርም ለዘራኸው ዘር ዝናብን ይሰጥሃል፤ ከመሬትም የሚገኘው ፍሬ ምርጥና የተትረፈረፈ ይሆናል። በዚያ ቀን ከብቶችህ በትልቅ ሜዳ ላይ ይሰማራሉ።


በዚያ ቀን የእግዚአብሔር ዛፍ ቅርንጫፍ ያማረና የከበረ ይሆናል፤ የምድሪቱም ፍሬ ከጥፋት ለተረፈው የእስራኤል ወገን ኵራትና ክብር ይሆናል።


ከያዕቆብ ዘር የሆኑትን፣ ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሱትን አመጣለሁ። የተመረጠው ሕዝቤ ይወርሳቸዋል፤ ባሪያዎቼም በዚያ ይኖራሉ።


ነገር ግን እኔ እግዚአብሔር እናገራለሁ፤ የምናገረውም ቃል ሳይዘገይ ይፈጸማል፤ እናንተ ዐመፀኛ ቤት ሆይ፤ የተናገርሁትን ሁሉ በዘመናችሁ እፈጽማለሁ” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”


ከፍ ባለው የእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎች ያወጣል፤ ፍሬ ያፈራል፤ ያማረም ዝግባ ይሆናል። የወፍ ዐይነት ሁሉ መኖሪያውን በዚያ ያደርጋል፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ ሥር ያርፋል።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እጄን አንሥቼ እምላለሁ፤ በዙሪያችሁ ያሉ ሕዝቦች ዘለፋ ይወርድባቸዋል።


የዱር እንስሳት ሆይ፤ አትፍሩ፤ መሰማሪያ መስኮቹ ለምልመዋልና፤ ዛፎቹ ፍሬአቸውን አፍርተዋል፤ የበለሱ ዛፍና የወይኑ ተክልም እጅግ አፍርተዋል።


ዐውድማዎቹ በእህል ይሞላሉ፤ መጥመቂያ ጕድጓዶችም በአዲስ የወይን ጠጅና በዘይት ተሞልተው ያፈስሳሉ።


ገርነታችሁ በሁሉ ዘንድ የታወቀ ይሁን፤ ጌታ ቅርብ ነው።


ምክንያቱም “ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ የሚመጣው እርሱ ይመጣል፤ አይዘገይም።


跟着我们:

广告


广告