Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 36:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ስለዚህ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከየአቅጣጫው ከብበው በመውጋት ስላጠቋችሁ፣ ለቀሩት ሕዝቦች ሁሉ ርስት ሆናችሁ፤ ለሕዝብም መሣቂያና መሣለቂያ ሆናችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰላጠፉአችሁ፥ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ ባድማ አድርገዋችኋልና፥ ውጠዋችኋልምና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የሕዝብ ማላገጫ ሆናችኋልና

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ብለህ ለእስራኤል ተራራዎች ትንቢት ተናገር አለኝ፦ የባዕድ አገር ሕዝቦች በሁሉም አቅጣጫ ምድራችሁን ስላፈራረሱትና በእርግጥም ባድማ ስላደረጉት አገራችሁ ለሌሎች ሕዝቦች ንብረት ሆነ። እናንተም የሰዎች መሳቂያና መሳለቂያ ሆናችኋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለቀ​ሩት አሕ​ዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ያሉ አሕ​ዛብ አዋ​ር​ደ​ዋ​ች​ኋ​ልና፤ ውጠ​ዋ​ች​ሁ​ማ​ልና፥ እና​ን​ተም የተ​ና​ጋ​ሪ​ዎች ከን​ፈር መተ​ረ​ቻና የአ​ሕ​ዛብ ማላ​ገጫ ሆና​ች​ኋ​ልና፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ስለዚህ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለቀሩት አሕዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙሪያችሁ ያሉ ባድማ አድርገዋችኋልና፥ ውጠዋችሁማልና፥ እናንተም የተናጋሪዎች ከንፈር መተረቻና የሕዝብ ማላገጫ ሆናችኋልና

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 36:3
33 交叉引用  

በልባቸው፣ “ዕሠይ! ያሰብነው ተሳካ! ዋጥ አደረግነውም” አይበሉ።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ጩኸቴን ስማ፤ ጸሎቴንም አድምጥ።


በቅጥሩ ደጅ ለሚቀመጡት የመነጋገሪያ ርእስ፣ ለሰካራሞችም መዝፈኛ ሆንሁ።


ሕዝቦች፣ “አምላካቸው የት አለ?” ለምን ይበሉ? የፈሰሰውን የአገልጋዮችህን ደም በቀል፣ ዐይናችን እያየ ሕዝቦች ይወቁት።


እኛም ለጎረቤቶቻችን መዘባበቻ፣ በዙሪያችንም ላሉት መሣቂያ መሣለቂያ ሆንን።


እንደ መቃብር፣ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱ፣ ከነሕይወታቸው በሙሉ እንዋጣቸው፤


ምድራቸው ባድማ፣ ለዘላለም መሣለቂያ ይሆናል፤ በዚያ የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፤ በመገረምም ራሱን ይነቀንቃል።


አንበሶች በርሱ ላይ አገሡ፤ በኀይለኛ ድምፅም ጮኹበት። ምድሩን ባድማ አድርገውበታል፤ ከተሞቹ ተቃጥለዋል፤ ወናም ሆነዋል።


በምድር መንግሥታት ሁሉ ፊት የሚያስጸይፉና የሚሰደቡ ይሆናሉ፤ በምበትናቸውም ስፍራ ሁሉ ለማላገጫና ለመተረቻ፣ ለመሣለቂያና ለርግማን አደርጋቸዋለሁ።


“ይህ ሕዝብ፣ ‘እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሁለቱን መንግሥታት ጥሏል’ እንደሚሉ አላስተዋልህምን? ሕዝቤን ንቀዋል፤ እንደ ሕዝብም አልቈጠሯቸውም።


“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላን፣ አድቅቆ ፈጨን፤ እንደ ባዶ ማድጋ አደረገን፤ እንደ ዘንዶ ዋጠን፣ እንደ ጣፋጭ በልቶን ሆዱን ሞላ፤ በኋላም አንቅሮ ተፋን፤


ሴዴቅያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ አንድ ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ የእናቱም ስም አሚጣል ነበረ፣ እርሷም የልብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።


የያዕቆብን መኖሪያ ሁሉ፣ ጌታ ያለ ርኅራኄ ዋጣቸው፤ የይሁዳን ሴት ልጅ ምሽጎች፣ በቍጣው አፈረሳቸው፤ መንግሥቷንና መሳፍንቷን፣ በማዋረድ ወደ ምድር ጣላቸው።


ጌታ እንደ ጠላት ሆነ፤ እስራኤልንም ዋጠ፤ ቤተ መንግሥቶቿን ሁሉ ዋጠ፤ ምሽጎቿን አፈራረሰ፤ በይሁዳ ሴት ልጅ፣ ልቅሶንና ሰቈቃን አበዛ።


ይህም ቀኑን ሙሉ በእኔ ላይ፣ ጠላቶቼ የሚያውጠነጥኑትና የሚያንሾካሹኩት ነው።


ሰው ይኖርባቸው የነበሩ ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም ወና ትሆናለች። በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።’ ”


“ ‘ሰላም ሳይኖር፣ “ሰላም አለ” እያሉ ሕዝቤን ያስታሉ፤ ሕዝቡ ካብ ሲሠራ እነርሱ በኖራ ይለስናሉ፤


በእኔ ላይ ታብየሃል፤ በድፍረትም በእኔ ላይ ተናግረሃል፤ እኔም ሰምቼዋለሁ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በሚቃጠል ቅናቴ በቀሩት ሕዝቦች ሁሉና በኤዶም ሁሉ ላይ ተናግሬአለሁ፤ ከልብ በመነጨ ደስታና በንቀት ተሞልተው የግጦሽ መሬቴን ይዘው ይበዘብዙት ዘንድ የራሳቸው ርስት አድርገውታልና።’


ጌታ ሆይ፤ ቀድሞ እንዳደረግኸው የጽድቅ ሥራህ ሁሉ፣ ከከተማህ ከኢየሩሳሌም፣ ከቅዱሱም ተራራህ ቍጣህን መልስ፤ በእኛ ኀጢአትና በአባቶቻችን በደል ምክንያት ኢየሩሳሌምና ሕዝብህ በዙሪያችን ባሉት ዘንድ መሣለቂያ ሆነዋል።


ምድሪቱ እነርሱ ለቅቀዋት ስለ ሄዱ ባዶ ትቀራለች፤ እነርሱ በሌሉበት ጊዜም ባድማ ሆና በሰንበቷ ትደሰታለች፤ ሕጌን በማቃለላቸውና ሥርዐቴን በመናቃቸው፣ የኀጢአታቸውን ቅጣት ይቀበላሉ።


በጥፋታቸው ቀን፣ በሕዝቤ በር መግባት የለብህም ነበር፤ በጥፋታቸው ቀን፣ በጭንቀታቸው መደሰት አልነበረብህም፤ በጥፋታቸው ቀን፣ ሀብታቸውን መዝረፍ አይገባህም ነበር።


ስማችንን ሲያጠፉ መልካም እንመልሳለን፤ እስከ አሁንም ድረስ የዓለም ጕድፍ፣ የምድር ጥራጊ ሆነናል።


እግዚአብሔር እንድትገባ በሚያደርግበት ምድር ለአሕዛብ ሁሉ መሸማቀቂያ፣ ማላገጫና መዘባበቻ ትሆናለህ።


跟着我们:

广告


广告