Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 36:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “የሰው ልጅ ሆይ፤ የእስራኤል ሕዝብ በገዛ ምድራቸው ይኖሩ በነበረበት ጊዜ በሥራቸውና በአኗኗራቸው አረከሷት፤ ጠባያቸውም በፊቴ፣ ሴት በወር አበባዋ ወቅት እንደምትረክሰው ዐይነት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት በምድራቸው በተቀመጡ ጊዜ በመንገዳቸውና በሥራቸው አረከሱአት፥ መንገዳቸው በፊቴ እንደ አደፍ ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “የሰው ልጅ ሆይ! የእስራኤል ሕዝብ በዚህች አገር ሲኖሩ በከንቱ አኗኗራቸውና በመጥፎ ሥራቸው ሁሉ ምድሪቱን አርክሰዋት ነበር፤ በፊቴም የነበራቸው አካሄድ፥ ሴት በወር አበባዋ ወቅት እንደ ርኩስ ሆና የምትታይበትን ያኽል ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 “የሰው ልጅ ሆይ! የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት በም​ድ​ራ​ቸው በተ​ቀ​መጡ ጊዜ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸ​ውና በጣ​ዖ​ታ​ቸው አረ​ከ​ሱ​አት፤ መን​ገ​ዳ​ቸ​ውም በፊቴ እንደ አደፍ ርኵ​ሰት ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የሰው ልጅ ሆይ፥ የእስራኤል ቤት በምድራቸው በተቀመጡ ጊዜ በመንገዳቸውና በሥራቸው አረከሱአት፥ መንገዳቸውም በፊቴ እንደ መርገም አደፍ ነበረ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 36:17
13 交叉引用  

እኔ፣ ፍሬዋንና በረከቷን እንድትበሉ፣ ለም ወደ ሆነ መሬት አመጣኋችሁ፤ እናንተ ግን መጥታችሁ ምድሬን አረከሳችሁ፤ ርስቴንም ጸያፍ አደረጋችሁ።


ተነሡና ከዚያ ሂዱ፤ ይህ ማረፊያ ቦታችሁ አይደለምና፤ ምክንያቱም ረክሷል፤ ክፉኛም ተበላሽቷል።


ምድሬን በድን በሆኑ አስጸያፊ ጣዖቶቻቸው ስላረከሱ፣ ርስቴንም በአሳፋሪ ነገሮች ስለ ሞሉ፣ ላደረጉት በደልና ኀጢአት ዕጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”


በቅሌቷም ምድሪቱን አረከሰች፤ ከድንጋይና ከግንድ ጋራ አመነዘረች፤


ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤ የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል።


ምድር በሕዝቧ ትረክሳለች፤ ሕግን ጥሰዋል፤ ሥርዐትን ተላልፈዋል፤ ዘላለማዊውንም ኪዳን አፍርሰዋል።


ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤


በተግባራቸው ረከሱ፤ በድርጊታቸውም አመንዝሮች ሆኑ።


跟着我们:

广告


广告