Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 35:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “ ‘እስራኤላውያን ቅጣታቸው እጅግ መራራ ከሆነ ደረጃ ላይ ደርሶ ፍዳቸውን በሚቀበሉበት ጊዜ፣ የጥንቱን ቂም ቋጥረህ ለሰይፍ ስለ ዳረግሃቸው፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የዘለዓለም ጥል ስላለህ በመጨረሻው የፍርዳቸው ጊዜ፥ በመከራቸው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “ ‘ለብዙ ጊዜ ከቈየው ጥላቻችሁ የተነሣ በኃጢአቱ ምክንያት በደረሰበት የመጨረሻ ቅጣትና በመከራው ጊዜ የእስራኤልን ሕዝብ ለሰይፍ አሳልፋችሁ ሰጣችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የዘ​ለ​ዓ​ለም ጠላት ሁነ​ሃ​ልና፥ በመ​ከ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ በኀ​ይ​ለ​ኛ​ይቱ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ቀጠሮ ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በሰ​ይፍ እጅ ጥለ​ሃ​ቸ​ዋ​ልና፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የዘላለም ጥል ስላለህ በመከራቸውም ጊዜ በኋለኛይቱ የኃጢአታቸው ቀጠሮ ጊዜ የእስራኤልን ልጆች በሰይፍ እጅ ጥለሃቸዋልና

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 35:5
15 交叉引用  

እግዚአብሔር ሆይ፤ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን፣ ኤዶማውያን እንዴት እንደ ዛቱ ዐስብ፤ ደግሞም፣ “አፍርሷት፤ ፈጽማችሁ አፈራርሷት!” አሉ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የኤዶም ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ ርኅራኄን በመንፈግ፣ ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፤ የቍጣውንም ነበልባል ሳይገድብ፣ መዓቱን ሳያቋርጥ አውርዶበታልና፤


“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ኤዶም የይሁዳን ቤት ተበቅሏልና፤ በዚህም በደለኛ ሆኗልና፤


የታለመልህ የሐሰት ራእይ፣ የተነገረልህ የውሸት ሟርት ቢኖርም፣ የግፍ ጽዋቸው በሞላ፣ ቀናቸው በደረሰ፣ መታረድ በሚገባቸው ክፉዎች፣ ዐንገት ላይ ይሆናል።


“ ‘አንተ የግፍ ጽዋህ የሞላ፣ የምትቀጣበት ቀን የደረሰ፣ ርኩስና ክፉ የእስራኤል መስፍን ሆይ፤


“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ፍልስጥኤማውያን በቂም ተነሣሥተው በክፉ ልብ ተበቅለዋልና፣ ይሁዳንም በቈየ ጠላትነት ለማጥፋት ፈልገዋልና፤


“ዐመፃን ለማስቆም፣ ኀጢአትን ለማስወገድ፣ በደልን ለማስተስረይ፣ ዘላለማዊ ጽድቅን ለማምጣት፣ ራእይንና ትንቢትን ለማተምና፣ እጅግ ቅዱስ የሆነውን ለመቀባት ስለ ሕዝብህና ስለ ተቀደሰችው ከተማህ ሰባ ሱባዔ ታውጇል።


ከዚያም ስለ እስራኤል ተራሮች፣ “ጠፍ ሆነዋል፤ ቦጫጭቀን እንድንበላቸው ለእኛ ተሰጥተዋል” ብለህ በንቀት የተናገርኸውን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሰማሁ በዚያ ጊዜ ታውቃለህ።


ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ፣ ለሰይፍም ስለት አሳልፈህ ስጥ፤ ሚስቶቻቸው የወላድ መካን፣ መበለትም ይሁኑ፤ ወንዶቻቸው በሞት ይቀሠፉ፤ ጕልማሶቻቸው በጦር ሜዳ ለሰይፍ ይዳረጉ።


ለሰይፍ ዐልፈው ይሰጣሉ፤ የቀበሮዎችም ምግብ ይሆናሉ።


“አንተ የሰው ልጅ ሆይ፤ ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤል ምድር እንዲህ ይላል፤ “ ‘ፍጻሜ! በአራቱም የምድሪቱ ማእዘን ፍጻሜ መጥቷል!


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በሚቃጠል ቅናቴ በቀሩት ሕዝቦች ሁሉና በኤዶም ሁሉ ላይ ተናግሬአለሁ፤ ከልብ በመነጨ ደስታና በንቀት ተሞልተው የግጦሽ መሬቴን ይዘው ይበዘብዙት ዘንድ የራሳቸው ርስት አድርገውታልና።’


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጋዛ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ በመውሰድ፣ ለኤዶም ሸጣለችና።


跟着我们:

广告


广告