ሕዝቅኤል 34:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 “የሰው ልጅ ሆይ፤ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፤ ትንቢት ተናገር፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ራሳቸውን ብቻ ለሚከባከቡ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች መንጋውን ማሰማራት አልነበረባቸውምን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፥ እረኞቹንም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለመገቡ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች በጎችን ማሰማራት አይገባቸውምን? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 “የሰው ልጅ ሆይ! በእስራኤል ጠባቂዎች ላይ ትንቢት ተናገርባቸው፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምለውን ሁሉ በትንቢት እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘መንጋውን መንከባከብና መጠበቅ ትታችሁ ራሳችሁን የምትጠብቁ እናንተ የእስራኤል እረኞች ወዮላችሁ! 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 “የሰው ልጅ ሆይ! ትንቢት ተናገር፤ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፤ እረኞችንም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች ራሳቸውን ያሰማራሉን? እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 የሰው ልጅ ሆይ፥ ትንቢት ተናገር፥ በእስራኤል እረኞች ላይ ትንቢት ተናገር፥ እረኞችንም እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ራሳቸውን ለሚያሰማሩ ለእስራኤል እረኞች ወዮላቸው! እረኞች በጎችን ያሰማሩ ዘንድ አይገባቸውምን? 参见章节 |