Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 33:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 “አንተን በሚመለከት፣ የሰው ልጅ ሆይ፤ የአገርህ ሰዎች በየቤቱ በርና ግድግዳ ሥር ሆነው ስለ አንተ ይነጋገራሉ፤ እርስ በራሳቸውም እንዲህ ይባባላሉ፤ ‘ኑና ከእግዚአብሔር የመጣውን መልእክት እንስማ።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 አንተም የሰው ልጅ ሆይ፥ የሕዝብህ ልጆች በቅጥር አጠገብና በቤቶቻቸው ደጃፍ ስለ አንተ ይናገራሉ፥ አንዱ ከአንዱ ጋር፥ እያንዳንዱ ከወንድሙ ጋር እንዲህ ይላሉ፦ ኑ ከጌታ የመጣው ቃል ምን እንደሆነ እንስማ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ሕዝቡ በከተማይቱ ቅጽር አጠገብና በየቤታቸው ደጃፍ የሚወያዩት ስለ አንተ ነው፤ እርስ በርሳቸውም ‘ኑና ከእግዚአብሔር ምን ቃል እንደ መጣ ሲነገር እንስማ’ ይላሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 “አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የሕ​ዝ​ብህ ልጆች በቅ​ጥር አጠ​ገ​ብና በቤት ደጆች ውስጥ ስለ አንተ ይና​ገ​ራሉ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም አንዱ ከአ​ንዱ ጋር፦ እን​ሂ​ድና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ውን ቃል እን​ስማ ይላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ የሕዝብህ ልጆች በቅጥር አጠገብና በቤት ደጆች ውስጥ ስለ አንተ ይናገራሉ፥ እርስ በርሳቸውም፥ አንዱ ከአንዱ ጋር፦ እንሂድና እግዚአብሔር ያለው ቃል ምን እንደ ሆነ እንስማ ብለው ይናገራሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 33:30
13 交叉引用  

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፤ በከንፈሩም ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ የሚያመልከኝም፣ ሰው ባስተማረው ሰው ሠራሽ ሥርዐት ነው።


ዕለት በዕለት ይፈልጉኛል፤ መንገዴን ለማወቅ የሚጓጉ ይመስላሉ፤ ትክክለኛውን ነገር እንደሚያደርግ፣ የአምላኩንም ትእዛዝ እንዳልተወ ሕዝብ ሁሉ፣ ተገቢ የሆነ ፍትሕ ይለምኑኛል፤ እግዚአብሔር ወደ እነርሱ እንዲቀርብ የሚወድዱም ይመስላሉ።


እነርሱም፣ “ሕግ ከካህናት፣ ምክር ከጠቢባን፣ ቃልም ከነቢያት ስለማይታጣ ኑና በኤርምያስ ላይ እንማከር፤ ኑ፤ በአንደበታችን እናጥቃው፣ እርሱ የሚናገረውንም ሁሉ አንስማ” አሉ።


እያንዳንዱ ለባልንጀራው ወይም ለዘመዱ፣ ‘እግዚአብሔር ምን መልስ ሰጠ?’ ወይም፣ ‘እግዚአብሔር ምን ተናገረ?’ ማለት ይገባዋል።


‘ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን፤ እርሱ ያለህን ሁሉ ንገረን፤ እኛም እንታዘዛለን’ ብላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር በላካችሁኝ ጊዜ ሕይወታችሁን የሚያጠፋ ስሕተት ፈጸማችሁ።


“የሰው ልጅ ሆይ፤ እነዚህ ሰዎች ጣዖቶቻቸውን በልባቸው አኑረዋል፤ ክፋታቸውን እንደ ማሰናከያ ድንጋይ በፊታቸው አስቀምጠዋል፤ ታዲያ ከእኔ እንዳች ነገር እንዲጠይቁ ልፍቀድላቸውን?


“የሰው ልጅ ሆይ፤ ለእስራኤል ሽማግሌዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሐሳቤን ልትጠይቁ መጣችሁን? በሕያውነቴ እምላለሁ ከእኔ ጠይቃችሁ እንድትረዱ አልፈቅድም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’


ቍርባናችሁን በምታቀርቡበት ጊዜ ልጆቻችሁን ለእሳት በመዳረግ እስከ ዛሬ ድረስ በጣዖቶቻችሁ ሁሉ እየረከሳችሁ ናችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ታዲያ የእኔን ሐሳብ እንድትጠይቁ ልፍቀድላችሁን? በሕያውነቴ እምላለሁ እንድትጠይቁኝ አልፈቅድም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ካደረጓቸው አስጸያፊ ነገሮች ሁሉ የተነሣ፤ ምድሪቱን ጠፍና ባድማ በማደርግበት ጊዜ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።’


“ ‘ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤


跟着我们:

广告


广告