Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 32:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በመቃብርም ውስጥ ኀያላኑ መሪዎች ስለ ግብጽና ስለ ተባባሪዎቿ፣ ‘ወደ ታች ወርደዋል፤ በሰይፍ ከተገደሉትና ካልተገረዙትም ጋራ በአንድ ላይ ተጋድመዋል’ ይላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የኃያላን አለቆች በሲኦል ውስጥ ከረዳቶቹ ጋር ሆነው፤ ወደ ታች ወርደዋል በሰይፍም ከተገደሉት ካልተገረዙት ጋር ተኝተዋል፤ ይሏቸዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ግብጻውያን ወደ ሙታን ዓለም በሚወርዱበት ጊዜ በሙታን ዓለም ውስጥ የነበሩ ታላላቅ አርበኞች አቀባበል ያደርጉላቸዋል፤ ሲቀበሉአቸውም ‘እናንተ ከተባባሪዎች ጋር ኑ ውረዱ! በጦርነት ከተገደሉት በእግዚአብሔር ከማያምኑ ጋር ተጋደሙ!’ ይሉአቸዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የኀ​ያ​ላን አለ​ቆች በሲ​ኦል ውስጥ ሆነው ከረ​ዳ​ቶቹ ጋር ይና​ገ​ሩ​ታል፤ በሰ​ይ​ፍም የተ​ገ​ደ​ሉት ያል​ተ​ገ​ረዙ ወር​ደው ተኝ​ተ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የኃያላን አለቆች በሲኦል ውስጥ ሆነው ከረዳቶቹ ጋር ይናገሩታል፥ በሰይፍም የተገደሉት ያልተገረዙ ወርደው ተኝተዋል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 32:21
11 交叉引用  

ሞት ሳይታሰብ ድንገት ይምጣባቸው፤ በሕይወት ሳሉ ወደ ሲኦል ይውረዱ፤ ክፋት በመካከላቸው ዐድራለችና።


ክፉዎች ተመልሰው ወደ ሲኦል ይወርዳሉ፤ እግዚአብሔርን የሚዘነጉ ሕዝቦችም ሁሉ እንደዚሁ።


ክፉዎች በክፋታቸው ይወድቃሉ፤ ጻድቃን ግን በሞት ጊዜ እንኳ መጠጊያ አላቸው።


ብርቱ ሰው እንደ ገለባ፣ ሥራውም እንደ ብልጭታ ይሆናል፤ ሁለቱም ዐብረው ይቃጠላሉ፤ እሳቱንም የሚያጠፋው የለም።”


“ ‘በዔድን ካሉት ዛፎች በውበትና በትልቅነት የሚወዳደርህ የትኛው ነው? ይሁን እንጂ አንተም እንደዚሁ ከዔድን ዛፎች ጋራ ከመሬት በታች ትወርዳለህ፤ በሰይፍ ከተገደሉት፣ ካልተገረዙትም መካከል ትጋደማለህ። “ ‘እንግዲህ ፈርዖንና ስፍር ቍጥር የሌለው ሕዝቡ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”


እንዲህም በላቸው፤ ‘እናንተ ከሌሎች የተለያችሁ ናችሁን? ውረዱ፤ ባልተገረዙትም መካከል ተጋደሙ።’


ከዘመናት በፊት ከወደቁት ከኀያላን ሰዎች፣ ከእነዚያ ሰይፋቸውን ተንተርሰው፣ ጋሻቸውንም ደረታቸው ላይ ይዘው ከነሙሉ ትጥቃቸው ወደ መቃብር ከወረዱት ጋራ አይጋደሙምን? የእነዚህ ተዋጊዎች ሽብር በሕያዋን ምድር ባሉት ያልተገረዙ ኀያላን ላይ ቢደርስም፣ የኀጢአታቸው ቅጣት በዐጥንታቸው ላይ ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告