ሕዝቅኤል 31:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 በእግዚአብሔርም የአትክልት ቦታ ያሉ ዝግባዎች፣ ሊወዳደሩት አልቻሉም፤ የጥድ ዛፎች፣ የርሱን ቅርንጫፎች አይተካከሉትም፤ የኤርሞን ዛፎችም፣ ከርሱ ቅርንጫፎች ጋራ አይወዳደሩም፤ በእግዚአብሔርም የአትክልት ቦታ ያለ ማንኛውም ዛፍ፣ በውበት አይደርስበትም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 በእግዚአብሔር ገነት የነበሩ ዝግባዎች አልሸፈኑትም፥ ጥዶችም ቅርጫፎቹን አይመስሉትም አስታ የሚባለውም ዛፍ ቅርጫፎቹን አይመሳሰሉትም ነበር፤ በእግዚአብሔር ገነት የነበረ ዛፍ ሁሉ በውበቱ አይመስለውም ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ያለው የሊባኖስ ዛፍ ሊወዳደረው አይችልም፤ የጥድ ዛፍም ቅርንጫፉን አያኽልም፤ የግራር ዛፎች ቅርንጫፍ ከእርሱ ቅርንጫፎች ጋር ሲወዳደር እንደ ኢምንት ነው። በእግዚአብሔር ገነት ውስጥ ካሉ ዛፎች መካከል አንዳቸው እንኳ እንደ እርሱ ያለ ውበት የላቸውም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 በእግዚአብሔር ገነት የነበሩ ዝግባዎች አይተካከሉትም፥ ጥዶችም ቅርንጫፎቹን፥ አስታ የሚባለውም ዛፍ ጫፎቹን አይመሳሰሉትም ነበር፤ የእግዚአብሔርም ገነት ዛፍ ሁሉ በውበቱ አይመስለውም ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 በእግዚአብሔር ገነት የነበሩ ዝግባዎች አላጨለሙትም፥ ጥዶችም ቅርጫፎቹን አስታ የሚባለውም ዛፍ ጫፎቹን አይመሳሰሉትም ነበር፥ የእግዚአብሔርም ገነት ዛፍ ሁሉ በውበቱ አይመሳሰለውም ነበር። 参见章节 |