Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 31:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ውሆች አበቀሉት፤ ጥልቅ ምንጮች አሳደጉት፤ ጅረቶቻቸው ፈሰሱ፤ የሥሮቹንም ዙሪያ ሁሉ አረሰረሱ፤ በመስኩ ላይ ወዳሉት ዛፎች ሁሉ፣ መስኖዎቻቸውን ለቀቁት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ውኆች አበቀሉት፥ ጥልቅ ውኃ አሳደገው፥ ወንዞቹም በተተከለበት ዙሪያ ይጐርፉ ነበር፥ ፈሳሾቹንም ወደ ምድረ በዳ ዛፍ ሁሉ ሰደደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እዚያም ዛፉን የሚያሳድገው በቂ ውሃ ነበረው፤ በመሬት ውስጥ ያለው ጥልቅ ውሃ ዛፉን ያሳድገዋል፤ ጅረቶችም በሜዳ በተተከሉ ዛፎች ዙሪያ ይፈስሳሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ውኃም አበ​ቀ​ለው፥ ቀላ​ይም አሳ​ደ​ገው፥ ወን​ዞ​ችም በተ​ተ​ከ​ለ​በት ዙሪያ ይጎ​ርፉ ነበር፤ ፈሳ​ሾ​ቹ​ንም ወደ ምድረ በዳ ዛፍ ሁሉ ላከ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ውኆችም አበቀሉት፥ ቀላይም አሳደገው፥ ወንዞችም በተተከለበት ዙሪያ ይጐርፉ ነበር፥ ፈሳሾቹንም ወደ ምድረ በዳ ዛፍ ሁሉ ሰደደ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 31:4
7 交叉引用  

የሕዝብ ብዛት የንጉሥ ክብር ሲሆን፣ የዜጎች ማነስ ግን ለገዥ መጥፊያው ነው።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ እሟገትልሻለሁ፣ በቀልሽንም እኔ እበቀልልሻለሁ፤ ባሕሯን አደርቃለሁ፣ የምንጮቿንም ውሃ።


“ ‘ከዚህ በኋላ ከምድሪቱ ዘር ወስዶ በመልካም ዐፈር አኖረው፤ ውሃ እንደ ልብ ባለበት ቦታ አጠገብ እንደ አኻያ ዛፍ ተከለው፤


“ ‘ደግሞም ትልቅ ክንፍ ያለውና አካሉ በላባ የተሸፈነ ሌላ ታላቅ ንስር ነበር። ያ የወይን ተክልም ውሃ ለማግኘት ከተተከለበት ቦታ ሥሩን ወደ እርሱ ሰደደ፤ ቅርንጫፉንም ወደ እርሱ ዘረጋ።


ቅርንጫፍ እንዲያወጣ፣ ፍሬ እንዲያፈራና ያማረ የወይን ተክል እንዲሆን በአጠገቡ ብዙ ውሃ ባለበት በመልካም መሬት ተተክሎ ነበር።’


ሰባቱን ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ እንዲህ አለኝ፤ “ና፤ በብዙ ውሆች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን አመንዝራ ፍርድ አሳይሃለሁ።


መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “አመንዝራዪቱ ተቀምጣባቸው ያየሃቸው ውሆች፣ ወገኖች፣ ብዙ ሰዎች፣ ሕዝቦችና ቋንቋዎች ናቸው።


跟着我们:

广告


广告