Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 30:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የግብጽ ምሽግ በሆነችው፣ በሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፤ ስፍር ቍጥር የሌለውን የቴብስን ሕዝብ አጠፋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የግብጽ ምሽግ በሆነችው በሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፤ የኖን ብዛት አጠፋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የግብጽ ዋና ምሽግ የሆነችው የፔሉስየም ከተማ የቊጣዬ መዓት እንዲወርድባት አደርጋለሁ፤ የቴብስን ብዙ ሕዝብ ሁሉ እገድላለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በግ​ብ​ፅም ኀይል በሲን ላይ መዓ​ቴን አፈ​ስ​ሳ​ለሁ፤ የሜ​ም​ፎ​ስ​ንም ብዛት አጠ​ፋ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በግብጽም ምሽግ በሲን ላይ መዓቴን አፈስሳለሁ፥ የኖእንም ብዛት አጠፋለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 30:15
6 交叉引用  

እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤ የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣ የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው።


መላው የእስራኤል ማኅበር ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን ከኤሊም ተነሥተው በኤሊምና በሲና መካከል ወደምትገኘው ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።


ጳትሮስን ባድማ አደርጋለሁ፤ በጣኔዎስ ላይ እሳት እለኵሳለሁ፤ በቴብስ ላይ ቅጣት አመጣለሁ።


በግብጽ ላይ እሳት አነድዳለሁ፤ ሲን በጭንቅ ትናጣለች፤ ቴብስ በማዕበል ትወሰዳለች፤ ሜምፊስ በማያቋርጥ ጭንቀት ውስጥ ትገባለች።


ቍጣውን ማን ሊቋቋም ይችላል? ጽኑ ቍጣውንስ ማን ሊሸከም ይችላል? መዓቱ እንደ እሳት ፈስሷል፤ ዐለቶችም በፊቱ ተሰነጣጥቀዋል።


ከዚያም ለሰባቱ መላእክት፣ “ሂዱ፤ ሰባቱን የእግዚአብሔር ቍጣ ጽዋዎች በምድር ላይ አፍስሱ” የሚል ታላቅ ድምፅ ከቤተ መቅደሱ ሰማሁ።


跟着我们:

广告


广告