Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 28:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በጥበብህና በማስተዋልህ፣ የራስህን ሀብት አከማቸህ፤ ወርቅም ብርም፣ በግምጃ ቤትህ አጠራቀምህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በጥበብህና በማስተዋልህ ሀብትን ለራስህ አግኝተሃል፥ ወርቅና ብርም በግምጃ ቤትህ ውስጥ ሰብስበሃል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በእርግጥ በጥበብህና በብልኀትህ ብዙ ሀብት አግኝተሃል፤ በግምጃ ቤትህም ብዙ ወርቅና ብር አግበስብሰሃል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በጥ​በ​ብ​ህና በማ​ስ​ተ​ዋ​ልህ ብል​ጽ​ግ​ናን ለራ​ስህ አግ​ኝ​ተ​ሃ​ልን? ወር​ቅ​ንና ብር​ንም በግ​ምጃ ቤትህ ውስጥ ሰብ​ስ​በ​ሃ​ልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በጥበብህና በማስተዋልህ ብልጥግናን ለራስህ አግኝተሃል ወርቅና ብርም በግምጃ ቤትህ ውስጥ ሰብስበሃል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 28:4
11 交叉引用  

የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤ እንደማይወጣ ረዥም ግንብም ይቈጥሩታል።


ሌላም ነገር ከፀሓይ በታች አየሁ፤ ሩጫ ለፈጣኖች፣ ውጊያም ለኀያላን አይደለም፤ እንጀራ ለጥበበኞች፣ ወይም ባለጠግነት ለብልኆች፣ ወይም ሞገስ ለዐዋቂዎች አይሆንም፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።


የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላልና፤ “ ‘ይህን ሁሉ ያደረግሁት በክንዴ ብርታት ነው፤ ደግሞም በጥበቤ አስተዋይ ነኝና። የመንግሥታትን ድንበር አፈረስሁ፤ ሀብታቸውን ዘረፍሁ፤ ነገሥታታቸውን እንደ አንድ ኀያል ሆኜ አዋረድሁ።


አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፤ በሸለቆችሽ ለምን ትመኪያለሽ? ለምንስ በፍሬያማ ሸለቆሽ ትኵራሪያለሽ? በብልጽግናሽ ተማምነሽ፣ ‘ማን ሊነካኝ ይችላል?’ ትያለሽ።


ሸቀጥሽ ከባሕር በወጣ ጊዜ፤ ብዙ ሕዝቦችን ታጠግቢ ነበር፣ በታላቅ ሀብትሽና ሸቀጥሽ፣ የምድርን ነገሥታት ታበለጥጊ ነበር።


እንዲህም ብለህ ተናገረው፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። “ ‘በወንዞችህ መካከል የምትተኛ አንተ ታላቅ አውሬ፣ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን፤ በአንተ ላይ ተነሥቻለሁ። “የአባይ ወንዝ የእኔ ነው፤ ለራሴም ሠርቼዋለሁ” ትላለህ።


በመንግሥትህ ውስጥ የቅዱሳን አማልክት መንፈስ ያለበት አንድ ሰው አለ፤ ይህ ሰው በአባትህ ዘመን እንደ አማልክት ጥበብና ማስተዋል፣ ዕውቀትም የሞላበት ሆኖ ተገኝቷል፤ አባትህ ንጉሥ ናቡከደነፆርም የጠንቋዮች፣ የአስማተኞች፣ የኮከብ ቈጣሪዎችና የመተተኞች አለቃ አደረገው።


ስለዚህ ለመረቡ ይሠዋል፤ ለወጥመዱም ያጥናል። በእነርሱ ተዝናንቶ ይኖራልና፤ ምግቡም ሠብቷል።


跟着我们:

广告


广告