Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 28:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በባዕዳን እጅ፣ ያልተገረዙትን ሰዎች አሟሟት ትሞታለህ፤ እኔ ተናግሬአለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በባዕዳን እጅ ያልተገረዙትን ሰዎች ሞት ትሞታለህ፤ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በውጪ አገር ሰዎች እጅ በእግዚአብሔር የማያምኑ ሰዎችን ሞት ትሞታለህ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።’ ”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የሚ​ወ​ጉ​ህም ሰዎች ብዙ​ዎች ናቸው፤ ያል​ተ​ገ​ረ​ዙ​ትን ሰዎች ሞት ትሞ​ታ​ለህ፤ የሚ​ገ​ድ​ሉ​ህም ሰዎች ያል​ተ​ገ​ረ​ዙት ናቸው፤ በእ​ጃ​ቸ​ውም ትሞ​ታ​ለህ። እኔ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በእንግዶች እጅ ያልተገረዙትን ሰዎች ሞት ትሞታለህ፥ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 28:10
19 交叉引用  

የሰሜንን ሕዝብ ሁሉ፣ አገልጋዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እጠራለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “በዚህች ምድርና በነዋሪዎቿም ላይ፣ በአካባቢዋም ባሉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ሰዎች የሚጸየፏቸውና የሚሣለቁባቸው፣ የዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ፤


ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ? ማንስ ይሰማኛል? እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው አልተገረዙምና፣ መስማት አይችሉም። በእግዚአብሔር ቃል ይሣለቃሉ፤ ደስም አይሰኙበትም።


ከከተማዪቱ አውጥቼ ለባዕዳን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ ፍርድንም አመጣባችኋለሁ።


የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤


ከአሕዛብ መካከል እጅግ ጨካኞች የሆኑትን ባዕዳን፣ በአንተ ላይ አመጣለሁ፤ በጥበብህ ውበት ላይ ሰይፋቸውን ይመዝዛሉ፤ ታላቅ ክብርህንም ያረክሳሉ።


ታዲያ በገዳዮችህ ፊት፣ “አምላክ ነኝ” ትላለህን? በገዳዮችህ እጅ ስትገባ፣ አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።


“ ‘በዔድን ካሉት ዛፎች በውበትና በትልቅነት የሚወዳደርህ የትኛው ነው? ይሁን እንጂ አንተም እንደዚሁ ከዔድን ዛፎች ጋራ ከመሬት በታች ትወርዳለህ፤ በሰይፍ ከተገደሉት፣ ካልተገረዙትም መካከል ትጋደማለህ። “ ‘እንግዲህ ፈርዖንና ስፍር ቍጥር የሌለው ሕዝቡ የሚደርስባቸው ይህ ነው፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”


እንዲህም በላቸው፤ ‘እናንተ ከሌሎች የተለያችሁ ናችሁን? ውረዱ፤ ባልተገረዙትም መካከል ተጋደሙ።’


በመቃብርም ውስጥ ኀያላኑ መሪዎች ስለ ግብጽና ስለ ተባባሪዎቿ፣ ‘ወደ ታች ወርደዋል፤ በሰይፍ ከተገደሉትና ካልተገረዙትም ጋራ በአንድ ላይ ተጋድመዋል’ ይላሉ።


ከአስጸያፊ ሥራችሁም ሌላ ምግብ፣ ሥብና ደም ስታቀርቡ ልባቸውንና ሥጋቸውን ያልተገረዙትን እንግዶች ወደ መቅደሴ በማስገባት ቤተ መቅደሴን አረከሳችሁ፤ ቃል ኪዳኔንም አፈረሳችሁ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ በልቡና በሥጋው ያልተገረዘ ባዕድ በእስራኤላውያን መካከል የሚኖር ቢሆንም እንኳ ወደ መቅደሴ አይግባ።


ይኸውም፣ እኔ ጠላት እንድሆንባቸውና ወደ ጠላቶቻቸው ምድር እንድሰድዳቸው ያደረገኝን ኀጢአት ቢናዘዙ፣ ያልተገረዘው ልባቸው ቢዋረድና ስለ ኀጢአታቸው የሚገባውን ቅጣት ቢቀበሉ፣


በኀጢአታችሁ እንደምትሞቱ ነግሬአችኋለሁ፤ እኔ እርሱ ነኝ ስላችሁ እኔ እርሱ እንደ ሆንሁ ካላመናችሁ፣ በኀጢአታችሁ ትሞታላችሁና።”


“እናንተ ልባችሁና ጆሯችሁ ያልተገረዘ! ዐንገተ ደንዳኖች ልክ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ሁልጊዜ ትቃወማላችሁ።


እኛ በእውነት የተገረዝን በእግዚአብሔር መንፈስ የምናመልክ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ የምንመካ፣ በሥጋም የማንታመን ነንና።


ዳዊት በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች፣ “ለመሆኑ ይህን ፍልስጥኤማዊ ገድሎ እንዲህ ያለውን ውርደት ከእስራኤል ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? ደግሞስ የሕያው እግዚአብሔርን ሰራዊት ይገዳደር ዘንድ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ እርሱ ማነው?” ሲል ጠየቀ።


ባሪያህ አንበሳውንም ድቡንም ገድሏል፤ ይህም ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ የሕያው እግዚአብሔርን ሰራዊት ተገዳድሯልና መጨረሻው ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告