Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 27:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ቀዛፊዎችሽ ከሲዶናና ከአራድ የመጡ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ፤ የራስሽ ጠቢባን የመርከቦችሽ መሪዎች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የሲዶናና የአርቫድ ነዋሪዎች ቀዛፊዎችሽ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የነበሩት ባለሙያዎችሽ የመርከቦችሽ መሪዎች ነበሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ቀዛፊዎችሽ ሲዶናና አርዋድ ከተባሉ ከተሞች የመጡ ናቸው፤ ጢሮስ ሆይ! ባለሙያዎችሽ የመርከብ አዛዦችሽ ነበሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አለ​ቆ​ችሽ በሲ​ዶና ይኖሩ ነበር፤ የአ​ራድ ሰዎ​ችም ቀዛ​ፊ​ዎ​ችሽ ነበሩ፤ ጢሮስ ሆይ! ጥበ​በ​ኞ​ችሽ በአ​ንቺ ዘንድ ነበሩ፤ የመ​ር​ከ​ቦ​ች​ሽም መሪ​ዎች ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የሲዶናና የአራድ ሰዎች ቀዛፎችሽ ነበሩ፥ ጢሮስ ሆይ፥ ጥበበኞችሽ በአንቺ ዘንድ ነበሩ የመርከቦችሽም መሪዎች ነበሩ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 27:8
13 交叉引用  

ከነዓንም፦ የበኵር ልጁ የሲዶን፣ የኬጢያውያን፣


የአራዴዎያውያን፣ የሰማሪናውያንና የአማቲያውያን አባት ነበረ። ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጐሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ፤


“ዛብሎን፣ በባሕር ዳር ይኖራል፤ የመርከቦች መጠጊያም ይሆናል፤ ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል።


“ስለዚህ የሊባኖስ ዝግባ እንዲቈረጥልኝ ትእዛዝ ስጥ፤ ሰዎቼ ከሰዎችህ ጋራ ዐብረው ይሠራሉ፤ የሰዎችህንም ደመወዝ አንተ በወሰንኸው እከፍልሃለሁ፤ ከሰዎቼ መካከል እንደ ሲዶናውያን ዕንጨት በመቍረጥ እስከዚህ የሠለጠነ ሰው አለመኖሩን ራስህም ታውቃለህና።”


በመርከቦቹም ላይ ከሰሎሞን ሰዎች ጋራ ዐብረው እንዲሠሩ፣ ኪራም ባሕሩን የሚያውቁ የራሱን መርከበኞች ላከ።


የአራዴዎያውያን፣ የሰማሪናውያንና የአማቲያውያን አባት ነበረ።


ካልኖ እንደ ከርከሚሽ፣ ሐማት እንደ አርፋድ፣ ሰማርያስ እንደ ደማስቆ አይደሉምን?


ስለ ደማስቆ፣ “ክፉ ወሬ ሰምተዋልና፣ ሐማትና አርፋድ ደንግጠዋል፤ እንደ ተናወጠ ባሕርም ታውከዋል፤ ልባቸውም ቀልጧል።


የአራድና የሔሌክ ሰዎች፣ ቅጥርሽን በየአቅጣጫው ጠበቁ፤ የገማድ ሰዎችም፣ በምሽግሽ ውስጥ ነበሩ። ጋሻቸውንም በቅጥርሽ ዙሪያ ሰቀሉ፤ ውበትሽንም ፍጹም አደረጉ።


መርከበኞችሽ ሲጮኹ፣ የባሕሩ ጠረፍ ይናወጣል።


“የሰው ልጅ ሆይ፤ ፊትህን ወደ ሲዶና አዙር፤ ትንቢትም ተናገርባት፤


እግዚአብሔርም በእስራኤል እጅ አሳልፎ ስለ ሰጣቸው ድል አደረጓቸው። በታላቂቱ ሲዶና መንገድ መጨረሻ እስከ ማስሮን፣ በስተ ምሥራቅም እስከ ምጽጳ ሸለቆ ድረስ አሳደዷቸው፤ ከእነርሱም በሕይወት የተረፈ አንድም ሰው አልነበረም።


跟着我们:

广告


广告