ሕዝቅኤል 27:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም32 ስለ አንቺ በዋይታ ያለቅሳሉ፤ እንዲህም እያሉ ሙሾ ያወርዳሉ፤ “ባሕር ውጦት የቀረ፣ እንደ ጢሮስ ማን አለ?” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 በልቅሶአቸውም ስለ አንቺ ሙሾን ያነሡልሻል፥ እንዲህም እያሉ በአንቺ ላይ ያሞሻሉ፦ በባሕር መካከል ጠፍቶ የቀረ እንደ ጢሮስ ማን ነው? 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 በሐዘናቸውም ስምሽን እያነሡ ያለቅሳሉ። ስለ አንቺም ሙሾ ያወጣሉ፤ እንዲህም ይላሉ፦ ‘በባሕር መካከል ጠፍታ እንደ ቀረች እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነው? 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 ልጆቻቸውም ሙሾን ያሞሹልሻል፤ በባሕር መካከል እንደ ታወከች እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነበር? ይላሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 በትካዜያቸውም ልቅሶ ያነሡልሻል፥ ስለ አንቺም ሙሾ ያሞሻሉ እንዲህም ይላሉ፦ በባሕር መካከል ጠፍቶ እንደ ቀረ እንደ ጢሮስ ያለ ማን ነው? 参见章节 |