Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 27:28 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 መርከበኞችሽ ሲጮኹ፣ የባሕሩ ጠረፍ ይናወጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ከመርከብ መሪዎች ጩኸት ድምፅ የተነሣ መሰማሪያዎች ይንቀጠቀጣሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 መርከበኞቹ ወደ ባሕር ሲሰጥሙ ያሰሙት ጩኸት በባሕር ዳር ያሉትን አገሮች አንቀጠቀጡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ከጩ​ኸ​ትሽ የተ​ነሣ የመ​ር​ከ​ብሽ መሪ​ዎች ፍር​ሀ​ትን ፈሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ከመርከብ መሪዎች ጩኸት ድምፅ የተነሣ በዙሪያሽ ያሉ ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 27:28
10 交叉引用  

አሕዛብ ይሰማሉ፤ ይንቀጠቀጡማል፤ የፍልስጥኤምን ሕዝብ ሥቃይ ይይዛቸዋል።


በባቢሎን ውድቀት ድምፅ ትናወጣለች፤ ጩኸቷም በሕዝቦች መካከል ያስተጋባል።


ከፈረሶቹ ብዛት የተነሣ ዐቧራ ይሸፍንሻል፤ ሰዎች ቅጥሮቿ ወደ ፈረሱ ከተማ እንደሚገቡ እርሱ በበሮችሽ በሚገባበት ጊዜ፣ ከፈረሶቹና ከጋሪዎቹ፣ ከሠረገሎቹም ድምፅ የተነሣ ቅጥሮችሽ ይናወጣሉ።


የመርከብ አደጋ በሚደርስበሽ ቀን፣ ሀብትሽ፣ ሸቀጥሽና የንግድ ዕቃሽ፣ መርከብ ነጂዎችሽ፣ መርከበኞችሽና መርከብ ሠሪዎችሽ፣ ነጋዴዎችሽና ወታደሮችሽ ሁሉ፣ በመርከብ ላይ ያሉትም ሁሉ፣ ወደ ባሕሩ ወለል ይዘቅጣሉ።


በጠረፍ አገር የሚኖሩ ሁሉ፣ በአንቺ ሁኔታ ተደናገጡ፤ ንጉሦቻቸው በፍርሀት ራዱ፤ ፊታቸውም ተለዋወጠ።


ወደ ጕድጓድ ከሚሄዱት ጋራ ወደ መቃብር ባወረድሁት ጊዜ ሲወድቅ በተሰማው ድምፅ አሕዛብ ደነገጡ። ከዚያም የዔድን ዛፎች ሁሉ፣ ምርጥና ልዩ የሆኑት የሊባኖስ ዛፎች፣ ውሃ የጠገቡትም ዛፎች ሁሉ ከምድር በታች ሆነው ተጽናኑ።


ከዚሁም ዐምስት መቶ ክንድ በዐምስት መቶ ክንድ፣ ዙሪያው ዐምሳ ክንድ ባዶ ቦታ ቀርቶ፣ ለመቅደሱ ይሁን።


የወታደሮቹ ጋሻ ቀይ ነው፤ ተዋጊዎቹ ቀይ ልብስ ለብሰዋል፤ ዝግጁ በሆኑበት ቀን፣ የሠረገሎቹ ብረት ያብረቀርቃል፤ የጦሩ ዘንግ ይወዛወዛል።


ያ ሁሉ ሀብት በአንድ ሰዓት ውስጥ ጠፋ።’ “የመርከብ አዛዦች ሁሉ፣ በመርከብ የሚጓዙ መንገደኞች ሁሉ፣ የመርከብ ሠራተኞችና ኑሯቸውን በባሕር ላይ የመሠረቱ ሁሉ በሩቅ ይቆማሉ።


跟着我们:

广告


广告