Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 27:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ቀዛፊዎችሽ፣ ወደ ጥልቁ ባሕር ይወስዱሻል፤ የምሥራቁ ነፋስ ግን፣ በባሕሩ መካከል ይሰባብርሻል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ቀዛፊዎችሽ ወደ ታላቅ ውኆች አመጡሽ፤ የምሥራቅ ነፋስ በባሕር ልብ ሰበረሽ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ቀዛፊዎችሽ አውጥተው ወደ ጥልቁ ባሕር ወሰዱሽ፤ ኀይለኛውም የምሥራቅ ነፋስ አንገላትቶ በባሕሩ ውስጥ ሰባበረሽ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 “ቀዛ​ፊ​ዎ​ችሽ ወደ ትልቁ ውኃ አመ​ጡሽ፤ የም​ሥ​ራቅ ነፋስ በባ​ሕር ውስጥ ሰበ​ረሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ቀዛፊዎችሽ ወደ ትልቁ ወኃ አመጡሽ፥ የምሥራቅ ነፋስ በባሕር ውስጥ ሰበረሽ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 27:26
13 交叉引用  

የምሥራቅ ነፋስ የተርሴስን መርከብ እንደሚሰባብር፣ አንተ አብረከረክሃቸው።


እንደ ሰማን፣ በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ከተማ፣ በአምላካችን ከተማ፣ እንዲሁ አየን፤ እግዚአብሔር ለዘላለም ያጸናታል። ሴላ


እናንተ የተርሴስ መርከቦች፣ ዋይ በሉ፤ ምሽጋችሁ ፈርሷል!


መወጠሪያ ገመድህ ላልቷል፤ ምሰሶው ጠብቆ አልተተከለም፤ ሸራው አልተወጠረም፤ በዚያ ጊዜ ታላቅ ምርኮ ይከፋፈላል፤ ዐንካሳ እንኳ ሳይቀር ምርኮ ይወስዳል።


ከምሥራቅ እንደሚወጣ ነፋስ፣ በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ፤ በመጥፊያቸው ቀን፣ ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።”


“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሰው እንደማይኖርባቸው ከተሞች ባድማ ሳደርግሽ፣ የውቅያኖስንም ውሃ በላይሽ አድርጌ በቀላይ ስሸፍንሽ፣


የመርከብ አደጋ በሚደርስበሽ ቀን፣ ሀብትሽ፣ ሸቀጥሽና የንግድ ዕቃሽ፣ መርከብ ነጂዎችሽ፣ መርከበኞችሽና መርከብ ሠሪዎችሽ፣ ነጋዴዎችሽና ወታደሮችሽ ሁሉ፣ በመርከብ ላይ ያሉትም ሁሉ፣ ወደ ባሕሩ ወለል ይዘቅጣሉ።


አሁን ግን በጥልቅ ውሃ ውስጥ፣ በባሕር ተንኰታኵተሻል፤ ጭነትሽና ተሳፋሪዎችሽ ሁሉ፣ ከአንቺ ጋራ ሰጥመዋል።


ወደ ጕድጓድ ያወርዱሃል፤ በጥልቁም ባሕር ውስጥ፣ በባሕሮችም ልብ ውስጥ አስከፊ ሞት ትሞታለህ።


ብዙም ሳይቈይ ግን፣ “ሰሜናዊ ምሥራቅ” የሚሉት ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ከደሴቲቱ ተነሥቶ ቍልቍል መጣባቸው።


ነገር ግን መርከቡ ከአሸዋ ቍልል ጋራ ተላትሞ መሬት ነካ፤ የፊተኛው ክፍሉም አሸዋው ውስጥ ተቀርቅሮ አልነቃነቅ አለ፤ የኋለኛው ክፍሉም በማዕበሉ ክፉኛ ስለ ተመታ ይሰባበር ጀመር።


መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “አመንዝራዪቱ ተቀምጣባቸው ያየሃቸው ውሆች፣ ወገኖች፣ ብዙ ሰዎች፣ ሕዝቦችና ቋንቋዎች ናቸው።


跟着我们:

广告


广告